በኤሌክትሪክ መሠረተ ልማት ስርቆት ከ239 ሚሊዮን ብር በላይ ኪሳራ ደረሰ

Date:

በ2018 ዓ.ም ባለፉት ዘጠኝ ወራት በኤሌክትሪክ መሠረተ ልማት ላይ በተፈጸሙ ስርቆቶች ሳቢያ ከ239 ሚሊዮን 420 ሽህ ብር በላይ ኪሳራ መድረሱን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት አስታወቀ።

ይህም በሀገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች እየተፈጸመ ያለው የወንጀል ድርጊት አሳሳቢ ደረጃ ላይ መደረሱን የሚያመላክት ነው ተብሏል።

ባለፉት ዘጠኝ ወራት ብቻ በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች 329 የመሠረተ-ልማት ስርቆት ወንጀሎች የተፈጸመ መሆኑን በአገልግሎቱ የሪጅኖች የሕግ አገልግሎት ድጋፍና አስተባባሪ ኃላፊ አቶ ወንድወሰን ጌታቸው ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ ገልፀዋል።

አክለውም እነዚህ ወንጀሎች የኃይልና የትራንስፎርመር ስርቆትን ጨምሮ ለኮሪዶር ልማት የተዘረጉ ኬብሎችን ያካተቱ ናቸው ብለዋል፡፡

የመሠረተ ልማት ስርቆቱ በሀገር ላይ እያደረሰ ያለው ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ስብራት ከፍተኛ መሆኑን ያብራሩት አቶ ወንድወሰን፤ የትራንስፎርመር ክፍሎችና የመዳብ ገመዶች በሚሰረቁበት ወቅት የኃይል አቅርቦት በድንገት የሚቋረጥ በመሆኑ የኅብረተሰቡ የዕለት ተዕለት እንቅስቃሴ በእጅጉ እያተስተጓጎለ እንደሚገኝም ገልጸዋል።

ተቋሙ መሠረተ ልማቶችን ለማስፋፋትና ለተጠቃሚዎች ለማድረስ ሊያውለው የነበረው ጠቃሚ ጊዜና ሀብት፣ የተሰረቁትን ለመተካት እንዲውል በመገደዱ የሀገሪቱን የልማት ፍጥነት በእጅጉ እየጎዳው እንደሚገኝም ተናግረዋል።

ወንጀለኞችን ለሕግ ለማቅረብና ተጠያቂ ለማድረግ ጥረቶች እየተደረጉ ቢሆንም፣ እነዚህ ጥብቅ ሕጎች በሥራ ላይ እያሉ እንኳ በየአካባቢው የሚፈጸመው ስርቆትና ውድመት አሁንም ሊቀንስ አለመቻሉን ገልጸዋል።

ችግሩን በዘላቂነት ለመቅረፍ የመንግሥት የሕግ አስከባሪ አካላት ርምጃ ብቻ በቂ አለመሆኑን የጠቆሙት ኃላፊው፤ ኅብረተሰቡ፣ የፀጥታ አካላትና እያንዳንዱ ዜጋ እነዚህን የልማት አውታሮች እንደ ሀብቱ በመቁጠር የመጠበቅና የመከላከል ኃላፊነቱን እንዲወጣ ጥሪ አቅርበዋል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ለ10 ምሁራን የሙሉ ፕሮፌሰርነት ማዕረግ ሰጥቷል

የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ አስተዳደር ቦርድ ጥቅምት 12 ቀን 2019...

ዳሸን ባንክ እና ሼባ ማይልስ የፕላቲንየም ብራንድ የማስተር ካርድ ይፋ አደረጉ

ዳሸን ባንክ እና ሼባ ማይልስ በኢትዮጵያ ለሚገኙ ደንበኞች የፕሪሚየም...

የአሜሪካ የደህንነት ኃላፊ ኢራንን አስጠነቀቁ

ቡሔራዊ ደህንነት ዳይሬክተር ጄይ ክላይተን አርብ ዕለት ኢራን በውጭ...

ኢትዮጵያ በግብርናው ዘርፍ  በአመት ከ1.1 ቢሊዮን ዶላር በላይ ታጣለች

85 በመቶ የሚሆነው የኢትዮጵያ ህዝብ በግብርናው ዘርፍ የተሰማራ ሲሆን...