በእድሜ ትንሹ የኒውዮርክ ዩኒቨርስቲ ተማሪ

Date:

ትውልዱ ከደቡብ እስያ የሆነው አሜሪካዊው ሱቦርኖ ይስሐቅ ባሪ ገና በሕጻንነቱ ነበር የተለያዩ የሂሳብ ቀመሮችን በመስራት ብዙዎችን ማስደነቅ የጀመረው፡፡

ባሪ ገና በ 2 ዓመቱ የፔሪዲክ ቴብልን ክፍሎች ማንበብ ይችል እንደነበር ተነግሯል፡፡

በ 4 ዓመቱ ደግሞ ከቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ በሂሳብ እና በሳይንስ ትምህርቶች ባሳየው ላቅ ያለ ውጤት የእውቅና ደብዳቤ ተሰጥቶታል።

ልዩ የትምህርት ችሎታው ከ4ኛ ወደ 8ኛ ክፍል ከዚያም ከ9ኛ ወደ 12ኛ ክፍል በአንድ ጊዜ እንዲዛወር አስችሎታል።

ሁለት መጽሐፍቶችን አዘጋጅቶ በሕንድ ውስጥ የኮሌጅ ትምህርቶችን እንዳስተማረ የኒውዮርክ ፖስት ዘገባ አመላክቷል።

የ12 ዓመቱ ሱቦርኖ ይስሐቅ ባሪ በኒውዮርክ ዩኒቨርስቲ የ200 ዓመት ታሪክ ውስጥ የመጀመሪያው በእድሜ ትንሹ ተማሪ ለመሆን በቅቷል፡፡

ዋና ትኩረቱን ሒሳብ ትምህርት በተከታይነት ፊዚክስን በማድረግ ትምህርቱን በመከታተል ላይ የሚገኘው ባሪ፤ ያለበት ደረጃ የሚፈልገው እና የሰራበት መሆኑን ባደረጋቸው በርከት ያሉ ቃለ ምልሶች ላይ ገልጿል፡፡

ባሪ “ዩኒቨርስቲ ተቀላቅየ መማሬ አዲስ አይደለም፤ ብዙ ልጆች በዚያ ውስጥ አልፈዋል” ሲልም ይናገራል፡፡

እ.ኤ.አ 2028 ላይ ፒ.ኤች.ዲ በማጠናቀቅ ትንሹ ፕሮፌሰር መሆን ከበርካታ እቅዶቹ መካከል መሆኑንም ያስረዳል፡፡

በኒውዮርክ ዩኒቨርስቲ በሚሰጠው የፊዚክስ ትምህርት መርሃ ግብር እድልን ለማግኘት በዓለም ላይ ያሉ ከ100ሺህ በላይ ተማሪዎች ሙከራ ያደርጋሉ፡፡

ከነዚህም መካከል ተቀባይነትን የሚያገኙት 13 በመቶ የሚሆኑት ብቻ መሆናቸውን ዩኒቨርስቲው ያጋራው መረጃ ያመላክታል፡፡

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

የዕጩው ስብዕና እና የዴሞክራሲያዊ እሴቶች ቁርጠኝነት

ግዮን መጽሔት :- ኢትዮጵያ በአሁኑ ወቅት ከምንም በላይ...

የካቮድ ኮሜርሻል “እፎይታ ኤክስፖ” ለሕዝብ ክፍት ነው

ካቮድ ኮሜርሻል ሪል ስቴት "ዘመናዊ የንግድ ቦታ፤ ከኪራይ እፎይታ”...

ደቡብ ሱዳን የነዳጅ ቅድመ-ክፍያ ውሎችን እንዳትፈጽም አገደ

የለንደን ፍርድ ቤት ደቡብ ሱዳን ከአሁን በኋላ አዳዲስ የነዳጅ...

” ከ140 በላይ ጠጠር አምራች ድርጅቶች ሙሉ በሙሉ ቆመዋል ” – ማህበሩ

" ካላቸው ቅሬታ ማቅረብ ይችላሉ። ግን መሬቱ መቼ እንደተወሰደባቸው...