በክረምቱ ድንገተኛ ጎርፍ ሊከሰት ስለሚችል ህብረተሰቡ ጥንቃቄ ያድርግ

Date:


በመጪዎቹ አስር ቀናት አልፎ አልፎ የሚኖረው ከባድ ዝናብ ለጎርፍ ተጋላጭ በሆኑ ተፋሰሶች ላይ ቅጽበታዊ ጎርፍ ሊያስከትል ስለሚችል ህብረተሰቡ ጥንቃቄ ሊያደርግ እንደሚገባ የኢትዮጵያ ሚቲዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት ገለፀ።

ኢንስቲትዩቱ እንዳስታወቀው በመጪዎቹ አስር ቀናት በደቡብ ምዕራብ፣ በምዕራብ፣ በሰሜን ምዕራብ እና በመካከለኛው የሀገሪቱ አካባቢዎች ላይ በበርካታ ቦታዎቻቸው ላይ ከመካከለኛ እስከ ከባድ መጠን ያለው እርጥበት ይኖራቸዋል።

በተጨማሪም በሰሜን ምስራቅ፣ በምስራቅ እና በደቡብ የሀገሪቱ አካባቢዎች ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው እርጥበት እንደሚኖራቸው መረጃዎች እንደሚያሳዩ ገልጿል።

የሚጠበቀው እርጥበት ለወቅቱ የግብርና ስራ እንቅሥቃሴ በአመዛኙ አዎንታዊ ሚና እንደሚኖረው ተመላክቷል፡፡

በሚኖረው እርጥበት ዘር መዝራት፣ ትርፍ ውሃን ከማሳ በማጠንፈፍ ማስወገድ፣ የአፈር መሸርሸር ስጋትን ለመቀነስ የጎርፍ መቀልበሻ ቦዮችን ማዘጋጀት እንደሚያስፈልግም ጠቁሟል።

ረባዳማ በሆኑ ማሳዎች የውሃ ማንጣፈፍ ስራዎች መስራትና የደረሱ የበልግ ሰብሎችን በሚኖሩ ደረቅ ቀናቶች መሰብሰብ እንዲሁም የሚገኘውን እርጥበት በመጠቀም የመኸር ዘር መዝራት እንደሚገባም አብራርቷል።

በቀጣዮቹ አስር ቀናት በሚኖረው ዝናብ በአብዛኛው ተፋሰሶች ላይ ከመጠነኛ እስከ ከፍተኛ መጠን ያለው የገፀ ምድር የውሃ ፍሰት እንደሚኖርም ተገልጿል።

በወንዝ ዳርቻ እንዲሁም ረግረጋማ አካባቢ የሚኖሩ ማህበረሰቦች ጥንቃቄ ማድረግ እንዳለባቸውና የሚመለከታቸው የዘርፉ አካላት አደጋን በመቀነስ መልካም እድሎችን እንዲጠቀሙም ተብራርቷል።

የጎርፍ መቀልበሻ ቦዮችን ማዘጋጀት፣ወራጅ ውሃን በእግርም ሆነ በቀላል ተሽከርካሪ ለማቋረጥ አለመሞከር፣ የጎርፍ የፍሳሽ መውረጃ ቦዮችን ማፅዳት፣ የዝናብ ውሃ ማሰባሰብና ማጠራቀም እንደሚገባ ተገልጿል ሲል የዘገበው ኢዜአ ነው፡፡

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ከ989 ሚሊዮን ብር በላይ የኮንትሮባንድ እቃዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ

የጉምሩክ ኮሚሽን ከግንቦት 27 እስከ ሰኔ 3 ቀን 2018...

“እኔ እስካለሁ ድረስ ኢራን የኑክሌር መሣሪያ ባለቤት አትሆንም!”

የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ ትናንት ሰኔ 5 ቀን...

አገር እንዲህ ዓይንህን ለአፈር ይባላል?

በተጀመረው የአለም ዋንጫ ደቡብ አፍሪካ በሜክሲኮ መሸነፏን ተከትሎ አፍሪካ...

አሜሪካ እና ኢራን የመጀመሪያ ደረጃ ስምምነት በ24 ሰዓት ውስጥ እንደሚፈራረሙ ፓኪስታን አስታወቀች

ዩናይትድ ስቴትስ እና ኢራን በሰላም ድርድሩ ማዕቀፎች ላይ መስማማታቸውን...