በጉዲፈቻ የተወሰዱ ኢትዮጵያውያን  ወደ ሃገራቸው ሊገቡ ነው

Date:

በጉዲፈቻ ተወስደው በተለያዩ የዓለም ሀገራት የሚኖሩ ትውልደ ኢትዮጵያውያንን ወደ ሀገራቸው የመመለስ ሥራ መጀመሩን የቱሪዝም ሚኒስቴር አስታውቋል።

ከስምንት ዓመታት በፊት በሚኒሶታ አሜሪካ በበጎ ፍቃደኛ ኢትዮጵያዉያን የተጀመረው  ንቅናቄ፣ አላማው በማደጎ የተወሰዱ ኢትዮጵያውያን  የማንነት ጥያቄን ምላሽ እንዲያገኝ ማድረግ  እንደሆነ ተመላክቷል።

ከዚህም በተጨማሪ ኢትዮጵያውያኑ ወደ ሀገራቸው ገብተው ኢንቨስትመንት  ላይ እንዲሳተፉና ሀገራቸውን የማስተዋወቅ ስራ እንዲያከናውኑ የማድረግ ዓላምም እንዳለው ተነግሯል፡፡

ኢትዮጵያውያኑን ለመቀበል የተዘጋጀው መድረክ ከጥቅምት 7 እስከ 14 ቀን  2018 ለሰባት ተከታታይ ቀናት እንደሚቆይ የተገለጸ ሲሆን፤ ስዊዲንን ጨምሮ በተለያዩ 15 የአለም ሀገራት የሚገኙት ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገር ቤት ይገባሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ከ989 ሚሊዮን ብር በላይ የኮንትሮባንድ እቃዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ

የጉምሩክ ኮሚሽን ከግንቦት 27 እስከ ሰኔ 3 ቀን 2018...

“እኔ እስካለሁ ድረስ ኢራን የኑክሌር መሣሪያ ባለቤት አትሆንም!”

የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ ትናንት ሰኔ 5 ቀን...

አገር እንዲህ ዓይንህን ለአፈር ይባላል?

በተጀመረው የአለም ዋንጫ ደቡብ አፍሪካ በሜክሲኮ መሸነፏን ተከትሎ አፍሪካ...

አሜሪካ እና ኢራን የመጀመሪያ ደረጃ ስምምነት በ24 ሰዓት ውስጥ እንደሚፈራረሙ ፓኪስታን አስታወቀች

ዩናይትድ ስቴትስ እና ኢራን በሰላም ድርድሩ ማዕቀፎች ላይ መስማማታቸውን...