“በጋዛ ተጨማሪ ግዛቶችን” እንዲወር እስራኤል ጦሯ  አዘዘች

Date:

የእስራኤል መከላከያ ሚንስትር ሃማስ የተቀሩትን ታጋቾች በሙሉ እስካልለቀቀ ድረስ ወታደሩ “በጋዛ ተጨማሪ ቦታዎችን እንዲወር” እንዲሁም የተወሰኑ ክፍሎችን በቋሚነት እንደሚይዝ ዛቱ።

እስራኤል ካትዝ የአገራቸው ወታደሮች በጋዛ የጀመሩትን የእግረኛ ጦር ጥቃት “በሕይወት ያሉ እና የሞቱት” ታጋቾች እስኪመለሱ ድረስ “አጠናቅረው እንደሚቀጥሉ” ተናግረዋል።

በጋዛ ከሚገኙት 59 ታጋቾች መካከል 24ቱ በሕይወት አሉ ተብሎ የሚታመን ሲሆን፣ ሁለተኛው የተኩስ አቁም ስምምነት ላይ የተደረገው ድርድር ውጤት ባለማሳየቱ እጣ ፈንታቸው አጠራጣሪ ሆኗል።

ከጥር ወር ጀምሮ ሲተገበር የነበረው የተኩስ አቁም ስምምነት በዚህ ሳምንት እስራኤል በጋዛ ላይ የጀመረችውን የምድር ዘመቻ እና የቦምብ ጥቃት ተከትሎ በይፋ አብቅቷል።

በጋዛ ሰርጥ ያለው ሁኔታን አስመልከቶ የተባበሩት መንግሥታት የፍልስጤም ስደተኞች ኤጀንሲ ባልደረባ ሳም ሮዝ “በመላው ጋዛ ፍፁም ተስፋ አስቆራጭ ነገሮች ናቸው የሚከሰቱት. . . በጣም፣ በጣም አሳዛኝ” ሲሉ ተናግረዋል።

እስራኤል እና አሜሪካ ሃማስን የተኩስ አቁም ስምምነቱን ለማራዘም የቀረበውን ሃሳብ ውድቅ አድርጓል ሲሉ ከስሰዋል።

ሃማስ በበኩሉ “ከአደራዳሪዎች ጋር በሙሉ ኃላፊነት እና ታማኝነት እየተወያየሁ ነው” ብሏል።

ይኹን እንጂ ካትዝ አርብ ዕለት በሰጡት መግለጫ “ሃማስ በእምቢታውን በቀጠለ ቁጥር በእስራኤል ስር የሚቆየው ግዛት እየጨመረ ይሄዳል” ብለዋል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

በከተማዋ ከ24 ሺህ በላይ ንቁ የግንባታ ፈቃድ ያላቸው ሳይቶች መኖራቸው ተገለፀ

በኮንስትራክሽን ዘርፍ የሚደርሰውን የህይወትና የንብረት ጉዳት ለመቀነስ የቁጥጥርና የግንዛቤ...

አትሌት ጉዳፍ ፀጋይ ለሕክምና በወሰደችው መድኃኒት ምክንያት ከውድድር ታገደች

የቀድሞዋ የሁለት ጊዜ የዓለየቀድሞዋፒዮኗ ኢትዮጵያዊቷ ጉዳፍ ፀጋይ ከውድድር በፊት...

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ እውቅና ሊሰጣቸው ነዉ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ እውቅና የሚያገኙት የጎርጎርጎረሳዉያኑ 2026 በሞሮኮ...