ብሄራዊ ባንክ የግማሽ ቢሊዮን ዶላር ጨረታውን አጠናቀቀ

Date:

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ ዛሬ ባካሄደው ግዙፍ የውጭ ምንዛሬ ጨረታ 500 ሚሊዮን ዶላር ለገበያ ያቀረበ ሲሆን፣ የቀረበው ፍላጎት ግን ካቀረበው በታች (455.29 ሚሊዮን ዶላር) ሆኖ ተመዝግቧል።

በዚህም ምክንያት በጨረታው የተሳተፉ 30 ባንኮች የጠየቁትን የውጭ ምንዛሬ ሙሉ በሙሉ ማግኘት ችለዋል።

በጨረታው አንድ ዶላር በአማካይ 153 ብር ከ25 ሳንቲም የተሸጠ ሲሆን፣ ከፍተኛው የመጫረቻ ዋጋ 154 ብር፣ ዝቅተኛው ደግሞ 152 ብር ሆኖ ተመዝግቧል።

ይህ የዛሬው ጨረታ ካለፈው ጥር ወር አፈጻጸም ጋር ሲነጻጸር መጠነኛ የዋጋ ቅናሽና የፍላጎት መረጋጋት የታየበት ነው። በጥር ወር በተደረገው ተመሳሳይ ጨረታ የአንድ ዶላር አማካይ ዋጋ 154 ብር ከ81 ሳንቲም የነበረ ሲሆን፣ በወቅቱ ከተሳተፉት 31 ባንኮች መካከል ዶላር ማግኘት የቻሉት 25ቱ ብቻ ነበሩ።

የዛሬው ውጤት ባንኮች የነበራቸው የውጭ ምንዛሬ ጥማት እየረገበ መምጣቱንና ብሄራዊ ባንክ ገበያውን ለማረጋጋት የያዘው ስትራቴጂ እየሰራ መሆኑን አመላካች ነው ተብሏል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

እንግሊዝ ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በታች ማህበራዊ ሚዲያ እንዳይጠቀሙ አገደች

የእንግሊዝ መንግሥት ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በታች የሆኑ ሕፃናትና ታዳጊዎች...

አሜሪካ 300 ሚሊዮን ዶላር ለኢራን ልትሰጥ ነው መባሉን ትራምፕ አስተባበሉ

አሜሪካ እና ኢራን ከስምምነት ከደረሱ በኋላ አሜሪካ እና አጋሮቿ...

ደህና ሁን! ሰሜ…ስሜ!

“ከልጅነታችን ጀምሮ ጥበብ አገናኝታን ፣ በግሽ አባይ የባህል ቡድን...

✌️ጀግናን ማክበርና መሸለም ጀግንነት ነው

✌️ከዕድሜው የገዘፈው የታሪኩ ጁዋር ጀግናውን ሙሉጌታ ከበደን የመዘከር የጀግንነት...