የኢትዮጲያ ብሔራዊ ቡድን ከፊቱ ለሚጠብቅዉ ወሳኝ የቅድመ ማጣሪያ ጨዋታ አስመልክቶ የብሔራዊ ቡድኑ ዋና አሰልጣኝ ዮሀንስ ሳህሌ በጁፒተር ሆቴል ጋዜጣዊ መግለጫን ሰጥተዋል።
የኢትዮጲያ ብሔራዊ ቡድን አሁን ያለበት ደረጃ የኢትዮጲያን ክብርና ዝና የማይመጥን በመሆኑ ይህንን ዉጤት ለመቀየር ፌዴሬሽኑም ፣አሰልጣኞችም እንዲሁም ተጫዋቾችም በቁጭት እየሰራን ነዉ ሲሉ አሰልጣኝ ዮሀንስ ሳህሌ ተናግረዋል።
በተለይም ደግሞ 120 ሚሊዮን ህዝብ ይዘን ዝቅተኛ ዉጤት ማስመዝገብ ለህዝቡ የማይመጥን በመሆኑ አሁን የምናደርገዉ ጨዋታ በራሱ ያስቆጫል ብለዋል አሰልጣኙ።
የኢትዮጲያ ብሔራዊ ቡድን የመጀመሪያ ጨዋታዉን የፊታችን መጋቢት 18 በሞሮኮ አልጀዲዳ ስታዲየም ከሳኦቶሜ እና ፕሪንሲፔ ጋር የሚያደርግ ሲሆን ነገ ወደ ስፍራዉ ሲያመራ የ13 ስዓት ጉዞም የሚያደርግ ይሆናል።
