የጃፓኗ ጠቅላይ ሚኒስትር ሳናኤ ታካኢቺ አገራቸው ሐሙስ ዕለት ከብሔራዊ የነዳጅ መጠባበቂያ ክምችቷ እንደምትለቅ አስታውቀዋል።
ጃፓን እዚህ ውሳኔ ላይ የደረሰችው የነዳጅ አቅርቦት እጥረት ስጋት እያደገ በመምጣቱ ነው።
አሜሪካ እና እስራኤል በኢራን ላይ ጦርነት መክፈታቸውን ተከተሎ ቴህራን ሆርሙዝ የባሕር ወሽመጥን በመዝጋቷ የዓለም የነዳጅ እና የተፈጥሮ ጋዝ ዋጋ አሻቅቧል።
ታካኢቺ በኤክስ ገጻቸው ላይ “ከሐሙስ ጀምሮ ከብሔራዊ ክምችታችን ነዳጅ መልቀቅ እንጀምራለን” ብለዋል።
ጃፓን ባለፈው ሳምነት “ለአገሪቱ በአጠቃላይ የሚያስፈልጋትን” ነዳጅ ለማቅረብ በሚል ከግል ክምችቶቿ መጠቀም ጀምራለች። ጃፓን የምትጠቀመው 95 በመቶ ነዳጅ የሚመጣው በሆርሙዝ ወሽመጥ ኩል ነው።
ይህ በእንዲህ እንዳለ ዛሬ ማክሰኞ በእስያ የአንድ በርሜል ብሬንት ድፍድፍ ነዳጅ ዘይት ዋጋ ከ100 ዶላር በላይ እየተሸጠ ነው።
