“ታሪኬ የሚጀምረው ከዚህ ነው!”

Date:

በ2026 የዓለም ዋንጫ ከካናዳ ብሔራዊ ቡድን ጋር ታሪካዊ ስኬት ማስመዝገብ የቻለውና በቅርቡ ወደ እንግሊዙ ኖርዊች ሲቲ ያመራው ትውልደ ኢትዮጵያዊው ኮከብ አሊ አህመድ፣ ለሶስት ቀናት በሚቆይ ይፋዊ ጉብኝት ወደ እናት ሀገሩ ኢትዮጵያ መጥቷል።

“መነሻዬም ሆነ ታሪኬ የሚጀምረው ከዚህ ነው” በማለት ወደ ሀገሩ በመመለሱ የተሰማውን ታላቅ ኩራት የገለጸው አሊ፣ በቆይታው የተለያዩ ታሪካዊና ተፈጥሯዊ የቱሪስት መስህቦችን እንደሚጎበኝ ተገልጿል።

የባሕልና ስፖርት ሚኒስትር ዴኤታ አቶ መኪዩ መሐመድ ለተጫዋቹ ደማቅ አቀባበል ያደረጉለት ሲሆን፣ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን መለያንም በስጦታ አበርክተውለታል።


የባሕልና ስፖርት ሚኒስቴር እንዲህ ያሉ ስኬታማ የዳያስፖራ ልጆች ወደ ሀገራቸው መመለስ ለኢትዮጵያ ወጣቶች ትልቅ ተስፋና አርአያ እንደሚሆን የገለጸ ሲሆን፣ አሊም ወደፊት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በዓለም ዋንጫ መድረክ ላይ እንደሚሳተፍ ያለውን አዎንታዊ ምኞት አጋርቷል።

በአሜሪካው MLS ባሳየው አስደናቂ ብቃት በጥር 2026 ወደ ኖርዊች ሲቲ ያመራውና ለካናዳ ብሔራዊ ቡድን 28 ጨዋታዎችን ያደረገው አሊ አህመድ፣ ይህ ጉብኝቱ በትውልደ ኢትዮጵያውያንና በሀገራቸው መካከል ያለውን ትስስር ይበልጥ የሚያጠናክር ታሪካዊ ክስተት ሆኖ አልፏል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ጄኤፍኤም 106.7 የሬዲዮ ጣቢያ ለ6 ወራት ታገደ

የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን ባደረገው የይዘት ክትትልና የኢንስፔክሽን ምልከታ...

ሱልጣን ቢን ኻሊፋ ግሩፕ በኢትዮጵያ በሆቴል ዘርፍ ሊሰማራ ነው

በተባበሩት ዐረብ ኤምሬቶች የኢፌዲሪ ልዩ መልዕክተኛና ባለሙሉ ሥልጣን አምባሳደር...

የአሜሪካ የታክስ ህግ የስፔንን የዓለም ዋንጫ ሽልማት ስጋት ላይ ጣለ

የስፔን ብሔራዊ ቡድን ከዓለም ዋንጫ ሊያገኘው ከሚችለው 50 ሚሊዮን...

ህወሓት ከሌሎች ተቃዋሚ ኃይሎች ጋር የሚደረግ ጥምረት አስፈላጊ መሆኑን ገለጸ

ሕዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ...