ትራምፕ በጃፓን ላይ እስከ 35 በመቶ ታሪፍ ለመጣል ዛቱ

Date:

የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ በሁለቱ አገራት መካከል የታሪፍ ስምምነት ላይ ለመድረስ የተቀመጠው ቀነ ገደብ ከመጠናቀቁ በፊት መግባባት ላይ የማይደረስ ከሆነ በጃፓን ላይ “30 ወይም 35 በመቶ” ታሪፍ እንደሚጥሉ ዛቱ።

ይህም በፈረንጆቹ ሚያዝያ 2 ቀን በዓለም ዙሪያ ባሉ አገራት ላይ ከፍተኛ የገቢ ቀረጥ ባወጁበት ወቅት ጃፓን ላይ ከተጣለው የ24 በመቶ ታሪፍ የበለጠ ይሆናል።

በአብዛኞቹ የንግድ አጋሮች ላይ ተጥሎ የነበረው ታሪፍ ከዋሽንግተን ጋር የሚደራደሩበት ጊዜ ለመስጠት በሚል ለ90 ቀናት ወደ 10 በመቶ ዝቅ ብሎ ነበር።

ይህ የእፎይታ ጊዜ በሚቀጥለው ሳምንት ረቡዕ የሚገባደድ ሲሆን ፕሬዝዳንት ትራምፕ ቀነ ገደቡን የማራዘም ሃሳብ እንደሌላቸው ተናግረዋል።

ትራምፕ ከቶኪዮ ጋር ስምምነት ላይ መድረስ ስለመቻሉ ጥራጣሬ አላቸው የቢቢሲ ዘገባ ነው።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ዶናልድ ትራምፕ ከኢራን ጋር የሚያደርጉት ድርድር እስኪጠናቀቅ ድረስ የተኩስ አቁሙ መራዘሙን አስታወቁ

ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ በፓኪስታን ጥያቄ መሠረት ከኢራን ጋር የገቡትንየተኩስ...

ለኢትዮጵያ የግብርና ዘርፍ የሚውል የ40 ሚሊዮን ዩሮ የገንዘብ ድጋፍ ተፈቀደ

የአውሮፓ ኢንቨስትመንት ባንክ የልማት ክንፍ የሆነው ኢአይቢ ግሎባል (EIB...

ሃይንከን በአልኮል መጠኑ ጠንከር ያለ ቢራ ለኢትዮጵያ ገበያ አስተዋወቀ

ሃይንከን ኢትዮጵያ በእለም አቀፍ ደረጃ ዝነኛ የሆነውን ዴሰፔራዶስ (Desperados)...