381 ትምህርት ቤቶች የ6ኛ ክፍል ተማሪዎቻቸውን በሙሉ አሳለፉ

Date:

በአዲስ አበባ የ6ኛ ክፍል ካስፈተኑ ትምህርት ቤቶች 381 ያህሉ ያስፈተኗቸውን ተማሪዎች ሙሉ በሙሉ አሳለፉ።

የከተማ አስተዳደሩ ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ዘላለም ሙላቱ የ6ኛ ክፍል ከተማ አቀፍ የፈተና ውጤት ይፋ አድርገዋል።

በወቅቱ እንደተናገሩት፤ ፈተናውን ከወሰዱ 79 ሺህ 34 ተማሪዎች ወስጥ 75 ሺህ 85 ተማሪዎች ከ50 በመቶ በላይ ውጤት በማምጣት ወደቀጣዩ የትምህርት እርከን ተሸጋግረዋል።

የትምህርት ዘመኑ የ6ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና የማለፊያ ውጤት 50 በመቶ እንዲሆን ተወስኗል ብለዋል።

በመንግሥት ትምህርት ቤቶች ትምህርታቸውን ከተከታተሉ 94 በመቶ በግል ትምህርታቸውን ከተከታተሉት ደግሞ 96 በመቶ የሚሆኑት ወደ ቀጣይ የትምህርት ክፍል የተሸጋገሩ ሲሆን፤ ከጊዜ ወደጊዜ በመንግሥትና በግል ትምህርት ቤቶች ያለው የውጤት ልዩነት እየጠበበ መምጣቱን አብራርተዋል።

በከተማ ደረጃ 734 ትምህርት ቤቶች ፈተና የሰጡ ሲሆን፤ 381 ትምህርት ቤቶች ያስፈተኗቸውን ተማሪዎች ሙሉ በሙሉ ማሳለፋቸው ገልፀዋል።

በከተማ ደረጃ ከ1እስከ 4 ከፍተኛ ውጤት ያመጡ ተማሪዎች ከመንግሥት ትምህርት ቤት መሆናቸውን የተነገሩት ዶክተር ዘላለም፤ ይህ የሚያሳየው በመንግሥት ትምህርት ቤቶች የተማሪዎች ሚገባን ጨምሮ መሠረተ ልማት ለሟሟላት የተሰሩ ሥራዎች ውጤታማ መሆናቸውን የሚያሰይ ነው ብለዋል።

በማታው መርሐ ግብር ትምህርታቸውን ከተከታተሉ ውስጥ 79 ነጥብ 6 በመቶ የሚሆኑት ወደ ቀጣዩ የትምህርት እርከን መሸጋገራቸውን አመልክተዋል።

አዲሱ ስርዓተ ትምህርት መሰረት በከተማ አስተዳደሩ የ6ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ከ2015 የትምህርት ዘመን ጀምሮ መሰጠቱን እንዲሁም በ2017 የትምህርት ዘመን ከባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት በመስራቱ  የተመዘገበው ውጤት አበራታች መሆኑን ገልፀዋል።

ዶክተር ዘላለም አያይዘውም በ2017 ዓ.ም የሒሳብና እንግሊዘኛ ትምህርትን ለማሻሻል ተግባራዊ የተደረገው ስትራቴጂ በተማሪዎች ውጤት መረጋገጡን በተጨማሪም የከተማ አስተዳደሩ በትምህርት ዘርፉ ላይ ባደረገው ትኩረት ውጤቱ መመዝገቡን ተናግረዋል።

ተፈታኝ ተማሪዎች ውጤታቸውን በትምህርት ቢሮው ድህረገጽ መመልከት እንደሚችሉ ተገልጿል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ዶናልድ ትራምፕ ከኢራን ጋር የሚያደርጉት ድርድር እስኪጠናቀቅ ድረስ የተኩስ አቁሙ መራዘሙን አስታወቁ

ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ በፓኪስታን ጥያቄ መሠረት ከኢራን ጋር የገቡትንየተኩስ...

ለኢትዮጵያ የግብርና ዘርፍ የሚውል የ40 ሚሊዮን ዩሮ የገንዘብ ድጋፍ ተፈቀደ

የአውሮፓ ኢንቨስትመንት ባንክ የልማት ክንፍ የሆነው ኢአይቢ ግሎባል (EIB...

ሃይንከን በአልኮል መጠኑ ጠንከር ያለ ቢራ ለኢትዮጵያ ገበያ አስተዋወቀ

ሃይንከን ኢትዮጵያ በእለም አቀፍ ደረጃ ዝነኛ የሆነውን ዴሰፔራዶስ (Desperados)...