ቻይና የአለማችንን ፈጣንና ጭነት እራሱ የሚያራግፍ  ግዙፍ መርከብ ይፋ አደረገች

Date:

የቻይና የመርከብ ግንባታ ኮርፖሬሽን በጂያንግዙ ግዛት የጫነውን ጭነት በራሱ የሚያራግፍ የአለማችንን ፈጣኑን መርከብ በይፋ ስራ ማስጀመሩን ሲጂቲኤን ዘግቧል።

ይህ ግዙፍ መርከብ 215 ሜትር ርዝመትና 42 ሜትር ስፋት ያለው ሲሆን፣ ከ41 ሺህ ቶን በላይ ክብደትና 29 ሺህ ኪዩቢክ ሜትር ጭነት የመያዝ ከፍተኛ አቅም እንዳለው ተገልጿል።

ይህ ዘመናዊ መርከብ በሰአት እስከ 12 ሺህ ቶን ጭነት የማራገፍ አስደናቂ ብቃት ያለው በመሆኑ በአለም የመጀመሪያው ፈጣን የመርከብ ስያሜን ተጎናጽፏል።

እንደነዚህ ያሉ የቴክኖሎጂ ምጥቀቶች በዓለም አቀፍ የባህር ላይ ጭነት እና ትራንስፖርት አገልግሎት ዘርፍ ላይ ከፍተኛ እና አዎንታዊ ለውጥ እንደሚያመጡ ተመላክቷል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ጄኤፍኤም 106.7 የሬዲዮ ጣቢያ ለ6 ወራት ታገደ

የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን ባደረገው የይዘት ክትትልና የኢንስፔክሽን ምልከታ...

ሱልጣን ቢን ኻሊፋ ግሩፕ በኢትዮጵያ በሆቴል ዘርፍ ሊሰማራ ነው

በተባበሩት ዐረብ ኤምሬቶች የኢፌዲሪ ልዩ መልዕክተኛና ባለሙሉ ሥልጣን አምባሳደር...

የአሜሪካ የታክስ ህግ የስፔንን የዓለም ዋንጫ ሽልማት ስጋት ላይ ጣለ

የስፔን ብሔራዊ ቡድን ከዓለም ዋንጫ ሊያገኘው ከሚችለው 50 ሚሊዮን...

ህወሓት ከሌሎች ተቃዋሚ ኃይሎች ጋር የሚደረግ ጥምረት አስፈላጊ መሆኑን ገለጸ

ሕዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ...