በአዲስ አበባ ታጥረው የተቀመጡ መሬቶች ላይ የመጨረሻ እርምጃ ሊወሰድ ነው

Date:

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ በ2018 በጀት ዓመት አፈጻጸም ግምገማ ማጠቃለያ መድረክ ላይ እንደገለጹት፣ ታጥረው ያለምንም አገልግሎት በተቀመጡ መሬቶች ላይ አስፈላጊው ማጣራት ተደርጎ በሚቀጥሉት ሁለት ወራት ውስጥ ጥብቅ እርምጃ ይወሰዳል።

ከንቲባዋ አዲስ አበባ መሬት ታጥሮ የሚቀመጥባት ከተማ እንዳልሆነችና ቀደም ሲል የተደረሰውን መግባባት ጥሰው አጥር አጥረው የሚያስቀምጡ አካላት ምንም ዓይነት ተጨማሪ ዕድል እንደማይሰጣቸው ገልጸዋል።

በተጨማሪም የከተማዋን ሰላምና ደህንነት ለማስከበር የተከናወኑ ማኅበረሰብ አቀፍ ሥራዎች ውጤታማ እንደነበሩና በርካታ አገር አቀፍና ዓለም አቀፍ ኩነቶች በሰላም እንዲጠናቀቁ ማስቻላቸውን አብራርተዋል።

በሌላ በኩል፣ የከተማዋን የገቢ አሰባሰብ ለማዘመን በተሠራው ሥራ የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ በአፍሪካ መልካም አሠራር አላቸው ከተባሉ 6 ከተሞች መካከል አንደኛ መውጣቱ ከአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን ጥናት መረጋገጡን ከንቲባዋ ይፋ አድርገዋል።

በጤናው ዘርፍም የባለሙያዎች ሥነ-ምግባር መሻሻሉንና ባለፉት አምስት ዓመታት የተከናወኑ የጤናና የመሠረተ ልማት ሥራዎች ከዚህ ቀደም ከተሠሩት ጋር ሲነፃፀሩ በእጥፍ እንደሚበልጡ በአልጋ ቁጥር፣ በሕክምና መሣሪያዎችና በተቋማት ይዘት መረጋገጡን አስረድተዋል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ለ10 ምሁራን የሙሉ ፕሮፌሰርነት ማዕረግ ሰጥቷል

የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ አስተዳደር ቦርድ ጥቅምት 12 ቀን 2019...

ዳሸን ባንክ እና ሼባ ማይልስ የፕላቲንየም ብራንድ የማስተር ካርድ ይፋ አደረጉ

ዳሸን ባንክ እና ሼባ ማይልስ በኢትዮጵያ ለሚገኙ ደንበኞች የፕሪሚየም...

የአሜሪካ የደህንነት ኃላፊ ኢራንን አስጠነቀቁ

ቡሔራዊ ደህንነት ዳይሬክተር ጄይ ክላይተን አርብ ዕለት ኢራን በውጭ...

ኢትዮጵያ በግብርናው ዘርፍ  በአመት ከ1.1 ቢሊዮን ዶላር በላይ ታጣለች

85 በመቶ የሚሆነው የኢትዮጵያ ህዝብ በግብርናው ዘርፍ የተሰማራ ሲሆን...