ቼልሲ የክለቦች ዓለም ዋንጫን አሸነፈ

Date:

የ2025ቱ የክለቦች ዓለም ዋንጫ ፍጻሜ ቼልሲን ከፒኤስጂ አገናኝቶ በሰማያዊዎቹ አሸናፊነት ፍጻሜውን አግኝቷል።

በመጀመሪያው አጋማሽ የጨዋታ ብልጫ የነበረው የሰሜን ለንደኑ ክለብ ቼልሲ በኮል ፓልመር (በ25ተኛ እ 30ኛ ደቂቃዎች) ሁለት እንዲሁም በአዲሱ ፈራሚያቸው ጃኦ ፔድሮ 43ኛ ደቂቃ ግቦች ሶስት ለ ባዶ በመመራት ለረፍት ወጥቷል።

በጨዋታው ከፍተኛ ግምት የተሰጠው የአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ እና የፈረንሳይ ሊግ አንድ ዋንጫ አሸናፊው ፔዤ፣ ምናልባትም የውድድሩን ደካማ አቋም ያሳየበት ሊሆን ይችላል የተባለ ጨዋታን አድርጓል።

በአንጻሩ የኤንሶ ማሬስካው ክለብ ተጨማሪ ግብ የሚሆኑ እድሎችን በሌላኛው አዲሱ ፈራሚያቸው ዴላፕ አማካይነት አግኝተው የፒኤስጂው ዳኖሮማ በሚገርም ሁኔታ አምክኗቸዋል።

ጃኦ ናቫስ በሰራው ጥፋት 85ኛው ደቂቃ ላይ በቀይ ካርድ መውጣቱን ተከትሎ፣ የፈረንሳዩ ክለብ የመጨረሻዎቹን ደቂቃዎች በአስር ተጫዋቾች ለመጨረስ ተገዷል።

በክለቦች ዓለም ዋንጫ ላይ ቼልሲ ያሳየው አቋም፣ በፕሪሚየር ሊጉ ጠንካራ ተፎካካሪ ሊሆን እንደሚችል ከወዲሁ አመላካች ነው እየተባለ ነው።

81 ሺ 118 ተመልካቾች በታደሙበት በሜትላይፍ ስታዲየም የፍጻሜ ጨዋታ ላይ የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ በክብር እንግድነት ተገኝተዋል።

NBCEthiopi

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

አክሊሉ ወንድሞቹ ለንባብ በቃ

በፀሐፌ ትዕዛዝ አክሊሉ ሀብተወልድ የልጅነት ታሪክ ላይ ያተኮረ ለታዳጊዎች...

የኢራን ተፈጥሮአዊ ምሽጎች እና ስትራቴጂካዊ ጥበብ

​ግዮን መጽሔት :- በመካከለኛው ምስራቅ የጂኦ-ፖለቲካ ትኩሳት...

ለአድዋ ድል መታሰቢያ በአሜሪካ ቀን ተሰየመ

በአሜሪካ፣ የፔንሲልቪኒያ ግዛት የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት፣ የአውሮፓዊያኑ 'መጋቢት...

ኢሎን መስክ የዓለማችን የመጀመሪያው ትሪሊዮነር ሆነ

ኢሎን መስክ የሀብት መጠኑ 1 ትሪሊዮን ዶላር ያለፈ የመጀመሪያው...