ናይል ኢንሹራንስ በ2017 በጀት ዓመት ከግብር በፊት 560.5 ሚሊዮን ብር ትርፍ አገኘሁ አለ

Date:

ይህም በቀዳሚው በጀት ዓመት ከተገኘው ትርፍ  ጋር ሲነጻጸር የ16.6 በመቶ ዕድገት አለው ብሏል፡፡

ኩባንያው በዓመታዊው ሪፖርቱ ከኢንቨስትመንት የተገኘው ገቢ መጨመር ለዕድገቱ አዎንታዊ አስተዋጽኦ አለው ሲል አስረድቷል፡፡

ናይል ኢንሹራንስ በበጀት ዓመቱ ከጠቅላላ፣ ከረዥም ጊዜ እና ከታካፉል መድን በድምሩ  1.26 ቢሊዮን ብር የመድን ገቢ ማግኘቱን ጠቅሷል።

ይህ ከቀዳሚው በጀት ዓመት ጋር ሲነጻጸር የ0.8 በመቶ ዕድገት አለው ብሏል፡፡

ኩባንያው በበጀት ዓመቱ በአጠቃላይ የከፈለው የመድን አገልግሎት ወጪ 986.7 ሚሊዮን ብር ደርሷል ሲል በሪፖርቱ አስፍሯል፡፡

ይህ ወጪ የካሳ ክፍያዎች፤ ከውልና ከካሳ ክፍያ ጋር ቀጥተኛ ግንኙነት ያላቸው የሥራ ክፍሎች ደመወዝ፣ እንዲሁም ለመድን ወኪሎችና ደላላዎች የተከፈለ የኮሚሽን ክፍያ ያካትታል ሲልም አስረድቷል፡፡

ወጪው ከቀዳሚው አመት ጋር ከተመዘገበው ጋር ሲነጻጸር የ54.4 በመቶ ጭማሪ ያሳያል፡፡

ለወጪው መጨመር በዋነኝነት የተሽከርካሪ የመለዋወጫ ዋጋ፣ የእጅ ሥራ ዋጋ፤ የክሬን አገልግሎት እና የሕክምና ወጪዎች በከፍተኛ መጠን በመጨመራቸው ምክንያት ነው ይላል ሪፖርቱ፡፡

ናይል ኢንሹራንስ በ2017 በጀት ዓመት  ከኢንቨስትመንት 363.3 ሚሊዮን  ብር አግኝቻለሁ ያለ ሲሆን በቀዳሚው ዓመት የተመዘገበው 249.3 ሚሊዮን ብር እንደነበር አስታውሷል፡፡

በተጠናቀቀው በጀት ዓመት አጠቃላይ የኩባንያው ዕዳ  3.5 ቢሊዮን ብር  ደርሷል ተብሏል።

ይህ ከቀዳሚው ዓመት ጋር  ሲነጻጸር የ45.8 በመቶ ዕድገት አሳይቷል፡፡

ይህም የጨመረበት ዋነኛ ምክንያት የመድን ኮንትራቶች ግዴታዎች(ላልተከፈሉ የካሳ ክፍያዎች የተያዘው መጠባበቂያ) በመጨመሩ  ነው ተብሏል፡፡

ኩባንያው ጠቅላላ ሀብቱ 5.7 ቢሊዮን ብር ፣የተከፈለ ካፒታሉ ደግሞ 1.25 ቢሊዮን ብር መድረሱን ከሪፖርቱ ላይ ተመልክተናል፡፡

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ለ10 ምሁራን የሙሉ ፕሮፌሰርነት ማዕረግ ሰጥቷል

የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ አስተዳደር ቦርድ ጥቅምት 12 ቀን 2019...

ዳሸን ባንክ እና ሼባ ማይልስ የፕላቲንየም ብራንድ የማስተር ካርድ ይፋ አደረጉ

ዳሸን ባንክ እና ሼባ ማይልስ በኢትዮጵያ ለሚገኙ ደንበኞች የፕሪሚየም...

የአሜሪካ የደህንነት ኃላፊ ኢራንን አስጠነቀቁ

ቡሔራዊ ደህንነት ዳይሬክተር ጄይ ክላይተን አርብ ዕለት ኢራን በውጭ...

ኢትዮጵያ በግብርናው ዘርፍ  በአመት ከ1.1 ቢሊዮን ዶላር በላይ ታጣለች

85 በመቶ የሚሆነው የኢትዮጵያ ህዝብ በግብርናው ዘርፍ የተሰማራ ሲሆን...