ኔታንያሁ ዌስት ባንክን ከእስራኤል ጋር እንዲቀላቀሉ ‘አልፈቅድም’ አሉ ትራምፕ

Date:

የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ቤንያሚን ኔታንያሁ በእስራኤል ወረራ ስር ያለው ዌስት ባንክን ወደ ግዛታቸው እንዲቀላቀሉ አልፈቅድም አሉ።

የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር አርብ ዕለት በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ጠቅላላ ጉባኤ ላይ ንግግር ከማድረጋቸው ቀደም ብለው በኦቫል ኦፊስ ለጋዜጠኞች ሃሳባቸው የሰጡት የአሜሪካው ፕሬዝዳንት፤ “እስራኤል ዌስት ባንክን እንድትቀላቀል አልፈቅድም…አይሆንም” ብለዋል።

ሰኞ ከኔታንያሁ ጋር የሚገናኙት ትራምፕ የጋዛ ስምምነት “በጣም ተቃርቧል” ሲሉ ገልጸዋል።

እስራኤል በጋዛ ያለውን ጦርነት እና የዌስት ባንክን ወረራ እንድታቆም ዓለም አቀፍ ጫና እየደረሰባት ነው።

የምዕራባውያን መንግሥታት ለፍልስጤም ነጻ አገርነት በይፋ ዕውቅና እየሰጡ ነው።

ቀኝ ዘመም እስራኤላውያን አካባቢውን መጠቅለል ይህንን ግፊት ለማስቆም አማራጭ መንገድ እንደሆነ ይመለከቱታል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

እንግሊዝ ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በታች ማህበራዊ ሚዲያ እንዳይጠቀሙ አገደች

የእንግሊዝ መንግሥት ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በታች የሆኑ ሕፃናትና ታዳጊዎች...

አሜሪካ 300 ሚሊዮን ዶላር ለኢራን ልትሰጥ ነው መባሉን ትራምፕ አስተባበሉ

አሜሪካ እና ኢራን ከስምምነት ከደረሱ በኋላ አሜሪካ እና አጋሮቿ...

ደህና ሁን! ሰሜ…ስሜ!

“ከልጅነታችን ጀምሮ ጥበብ አገናኝታን ፣ በግሽ አባይ የባህል ቡድን...

✌️ጀግናን ማክበርና መሸለም ጀግንነት ነው

✌️ከዕድሜው የገዘፈው የታሪኩ ጁዋር ጀግናውን ሙሉጌታ ከበደን የመዘከር የጀግንነት...