አለም አቀፉ የፈርኒቸር ተቋም ወደ ኢትዮጵያ ገበያ ገባ

Date:

ተቀማጭነቱ አሜሪካ ሀገር ያደረገው አሽሊ ፈርኒቸር በዩስራ ሆምስ አማካኝነት ወደ ኢትዮጵያ ገበያ ገብቷል።

መቀመጫውን በዊስኮንሲን አሜሪካ የሆነው አሽሊ ፈርኒቸር ኢንዱስትሪዎች በዓለም ላይ ትልቁ የቤት ዕቃዎች አምራች እንደሆነ ተገልጿል።

በ155 ሀገራት ከ30ሺ በላይ ሰራተኞች ያሉት አሽሊ ፈርኒቸር ሐምሌ 4/2017 ዓ.ም ምርቶቹን በኢትዮጵያ ገበያ ለማቅረብ የመግባቢያ ስምምነት አድርጓል።

በኢትዮጵያ ቅንጡ ፈርኒቸሮችን በማምረት ከሚታወቀው ዩስራ ሆም ጋር የመግባቢያ ስምምነት ያደረገም ሲሆን በቅርቡ የተቋሙ የፈርኒቸር ውጤቶች በኢትዮጵያ ገበያ ይገባሉ ተብሏል።

በዚህ ልዩ አጋርነት ስምምነት መሰረት ዩስራ ሆም ዓለም አቀፍ ደረጃቸውን የጠበቁ የአሽሊ ፈርኒቸር ውጤቶችን በቀጥታ ወደ ኢትዮጵያ ገበያ በማስገባት እንደሚሸጥ የዩስራ ሆም መስራች እና ስራ አስኪያጅ ዩስራ ኑርሁሴን ገልጿለች።

በመግባቢያ ስምምነቱ ላይ የአሜሪካው አምባሳደር አርቪን ማሲንጋ ጨምሮ በርካታ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝቷል።

ዩስራ ሆም ከተመሰረተ አምስት አመታትን ያስቆጠረ ሲሆን ለመንግስት መስሪያ ቤቶች እና ለግል ተቋማት ቅንጡ ፈርኒቸር ውጤት ሲያቀርብ ቆይቷል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

በከተማዋ ከ24 ሺህ በላይ ንቁ የግንባታ ፈቃድ ያላቸው ሳይቶች መኖራቸው ተገለፀ

በኮንስትራክሽን ዘርፍ የሚደርሰውን የህይወትና የንብረት ጉዳት ለመቀነስ የቁጥጥርና የግንዛቤ...

አትሌት ጉዳፍ ፀጋይ ለሕክምና በወሰደችው መድኃኒት ምክንያት ከውድድር ታገደች

የቀድሞዋ የሁለት ጊዜ የዓለየቀድሞዋፒዮኗ ኢትዮጵያዊቷ ጉዳፍ ፀጋይ ከውድድር በፊት...

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ እውቅና ሊሰጣቸው ነዉ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ እውቅና የሚያገኙት የጎርጎርጎረሳዉያኑ 2026 በሞሮኮ...