ናይጄሪያዊው ቢሊየነር አሊኮ ዳንጎቴ ከዳንጎቴ ሲሚንቶ ሊቀመንበርነት መልቀቃቸውን ይፋ አድርገዋል።
ይህ ውሳኔ ከዚህ ቀደም ከሌላኛው ድርጅታቸው ከለቀቁ በኋላ የመጣ ሲሆን፣ ኩባንያው የዳንጎቴ መልቀቅ አስቀድሞ ታቅዶ በነበረው የአመራር ሽግግር ሂደት አካል እንደሆነ አስታውቋል።
በአቶ ዳንጎቴ ምትክ ኢማኑኤል ኢካዞቦህ የዳንጎቴ ሲሚንቶ አዲስ ሊቀመንበር ሆነው ተሹመዋል።
ዳንጎቴ ሲሚንቶ በአፍሪካ ትልቁ የሲሚንቶ ፋብሪካ ሲሆን፣ ናይጄሪያን ከሲሚንቶ አስመጪነት ወደ ትልቁ ላኪነት በመቀየር ትልቅ አስተዋጽኦ አድርጓል።
ድርጅቱ በዓመት 48.6 ሚሊዮን ሜትሪክ ቶን ሲሚንቶ ያመርታል።
በኢትዮጵያ የሚገኘው የዳንጎቴ ሲሚንቶ ፋብሪካ በቅርቡ 400 ሚሊዮን ዶላር የሚያወጣ የማስፋፊያ ፕሮጀክት እንደሚካሄድበት ተገልጿል።
ይህ መስፋፋት የፋብሪካውን የዓመት ምርት ከ5 ሚሊዮን ቶን በላይ ከማድረጉም በላይ ለተጨማሪ 25,000 ሰዎች የስራ እድል እንደሚፈጥር ይጠበቃል።
