አሜሪካና ቻይና አቅደውት የነበረዉን የታሪፍ ጭማሪ ለ90 ቀናት ለማራዘም መስማማታቸዉ ተገለጸ፡፡ ይሄ የተሰማው ሁለቱ ሀገራት በጉዳዩ ላይ በጋራ በሰጡት መግለጫ ነው።
ሁለቱ ሀገራት ከስምምነት የደረሱትም ለተጨማሪ ሶስት ወራት ታሪፍን ላለመጣል አስቀምጠውት የነበረው ቀነ ገደብ አልቆ የመጨረሻው ቀን ላይ ደርሰው ነዉ።
ሀገራቱ ከስምምነት ባይደርሱ አሜሪካ ከቻይና በምታስገባቸው ምርቶች ላይ የምትጥለውን ታሪፍ እስከ 145 በመቶ ከፍ ታደርግ የነበረ ሲሆን፤ ቻይና በአሜሪካ ላይ የምትጥለው የታሪፍ መጠን ግን አልታወቀም ነበር።
ይሁን እንጂ አሜሪካ ከዚህ በፊት በቻይና ዕቃዎች ላይ ጥላ የነበረዉ የ30 በመቶ የታሪፍ ጭማሪና ቻይናም በአሜሪካ ምርቶች ላይ የጣለችዉ የ10 በመቶ የታሪፍ ጭማሪ እንደሚቀጥል ተዘግቧል።
ጋዜጣ+
