አሜሪካ በሩሲያ ሳይበር ጥቃት እየታመሰች ነው

Date:


የሩሲያ የሳይበር ጥቃት አድራጊዎች የአሜሪካ የፌዴራል ፍርድ ቤት የኮምፒውተር ስርዓቶችን ዘልቀው በመግባት ለአመታት መረጃ ሲሰርቁ እንደነበር ተገለጸ።


ይህ የደህንነት ጥሰት ለአሜሪካ ብሔራዊ ደህንነት አስጊ እንደሆነ እና የፌደራል ፍርድ ቤቶች ሰነዶችን እንደሚያጋልጥ ተነግሯል።

የአሜሪካ የፍትህ አካላት እና የደህንነት ባለሥልጣናት እንደዘገቡት ከሆነ፣ ተጠርጣሪዎቹ የሩሲያ የሳይበር ጠላፊዎች ለአራት አመታት የፌዴራል ፍርድ ቤቶችን ሲስተም ውስጥ በመግባት መረጃ ሲሰበስቡ ነበር ብለዋል።

ይህ ጥቃት የአሜሪካን የጸረ-መረጃ መረብ ዘመቻ እንደሚያደናቅፍና የሩሲያ ብልሹ አሰራርን የሚያጋልጡ ሚስጥራዊ መረጃዎችን ሊያጋልጥ እንደሚችል የደህንነት ባለሙያዎች ይገልጻሉ።

ባለፈው ሳምንት ይህ መረጃ ይፋ ከሆነ በኋላ፣ የአሜሪካ የፍትህ ዲፓርትመንት እና የፌዴራል ፍርድ ቤቶች የሁኔታውን አሳሳቢነት በመገንዘብ አስፈላጊውን እርምጃ እየወሰዱ ነው ተብሏል።

የሳይበር ጥቃቱ እስካሁን በየትኞቹ ፍርድ ቤቶች ላይ ጉዳት እንዳደረሰ በግልጽ ባይገለጽም፣ የሩሲያ ተሳትፎ መኖሩ ግን የሩሲያ እና የአሜሪካን የፖለቲካ ውጥረት ሊያባብስ ይችላል ተብሏል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

በከተማዋ ከ24 ሺህ በላይ ንቁ የግንባታ ፈቃድ ያላቸው ሳይቶች መኖራቸው ተገለፀ

በኮንስትራክሽን ዘርፍ የሚደርሰውን የህይወትና የንብረት ጉዳት ለመቀነስ የቁጥጥርና የግንዛቤ...

አትሌት ጉዳፍ ፀጋይ ለሕክምና በወሰደችው መድኃኒት ምክንያት ከውድድር ታገደች

የቀድሞዋ የሁለት ጊዜ የዓለየቀድሞዋፒዮኗ ኢትዮጵያዊቷ ጉዳፍ ፀጋይ ከውድድር በፊት...

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ እውቅና ሊሰጣቸው ነዉ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ እውቅና የሚያገኙት የጎርጎርጎረሳዉያኑ 2026 በሞሮኮ...