አሜሪካ በኤርትራ የሚገኘውን ጨምሮ 10 ኤምባሲዎቿን ልትዘጋ ነው

Date:

  • ከሚዘጉት ኤምባሲዎች 6ቱ በአፍሪካ የሚገኙ ናቸው ተብሏል

የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መ/ቤት በኤርትራና ደቡብ ሱዳን የሚገኙትን ጨምሮ 10 ኤምባሲዎቹን ለመዝጋት ማቀዱ ተገለጸ።

ከኤምባሲዎቹ በተጨማሪ 17 ቆንስላዎቹንም ለመዝጋት ማቀዱን ኒውዮርክ ታይምስ ጋዜጣ ዘግቧል።

የውጭ ጉዳይ መ/ቤቱ እንዲዘጉ ባቀዳቸው ኤምባሲዎች ይከናወኑ የነበሩ ስራዎችን በአጎራባች ሀገራት ኤምባሲዎች ለማከናወን ማቀዱንም ዘገባው ጠቁሟቋል።

የኤምባሲዎቹና ቆንስላዎቹ መዘጋት የትራምፕ አስተዳደር የፌደራል መንግሥትን ባጀት ለመቀነስ እየወሰደ ያለው እርምጃ አካል ነው ተብሏል።

አሜሪካ ለመዝጋት ካቀደቻቸው አስር ኤምባሲዎች መካከል ስድስቱ በአፍሪካ የሚገኙ መሆናቸው ተጠቁሟል፡፡

በሶማሊያ ሞቃዲሾ የሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲም ሙሉ በሙሉ እንዲዘጋ፣ ካልሆነ ደግሞ ሰራተኞቹ በከፍተኛ ቁጥር እንዲቀነሱ ሃሳብ መቅረቡን ዘገባው አመላክቷል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ግዮን መጽሔት በዛሬ ዕትሟ

ግዮን መጽሔት ዛሬ ቅዳሜ ነሔሴ 16 2018 ዓ.ም ገበያ...

ቱርክ ቤንያሚን ኔታንያሁ ላይ የእስር ማዘዣ አወጣች

ቱርክ የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ ላይ ዓለም አቀፍ...

በመቀለ የሚካሄደው የአሸንዳ በዓል የመክፈቻ ሥነ ሥርዓት ተሰረዘ

በትግራይ በርካታ ታዳሚ በሚገኝበት በየዓመቱ የሚከበረው የአሸንዳ ባህላዊ በዓል...

የኢትዮጵያ ፖስታ 3 ሺሕ የሚጠጉ ቅርንጫፎቹን ወደ ባንክ ኤጀንትነት ለመቀየር እንቅስቃሴ ጀመረ

የኢትዮጵያ ፖስታ በመላ ሀገሪቱ የሚገኙ 3 ሺሕ በሚጠጉ ቅርንጫፎቹ...