ከበሮ፣ ጸናጽል፣ መቋሚያ በቤተ ክርስቲያን ባለቤትነት በሕግ ተመዝገቡ

Date:

የቅድስት ቤተ ክርስቲያ የዜማ ንዋያተ ቅዱሳት እና ከ10 በላይ ቅዱሳት መጻሕፍት አእምሯዊ ንብረት ሆነው መመዝገባቸው ን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሕዝብ ግኑኝነት መምሪያ ዘገባ ያስረዳል።

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የዜማ ንዋያተ ቅዱሳት የሆኑት ከበሮ፣ ጸናጽል፣ መቋሚያና እንዲሁም ከ10 በላይ ቅዱሳት መጻሕፍት በኢትዮጵያ አእምሯዊ ንብረት ባለሥልጣን በቅጂና ተዛማች መብቶች መመዝገባቸው ተገልጿል፡፡

ሚያዝያ 3 ቀን 2017 ዓ.ም የዜማ ንዋያተ ቅዱሳቱ እና ቅዱሳት መጻሕፍቱ ተመዝግበው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አእምሯዊ ንብረት መሆናቸው ከባለሥጣኑ በወጣው ደብዳቤ ተረጋግጧል።

የመምሪያው ኃላፊ መልአከ ሰላም ዳዊት ያሬድ እንደተናገሩት ከዚህ ቀደም በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የቅርስ ጥበቃ ቤተ መጻሕፍት ወመዘክር መምሪያ በአእምሯዊ ንብረት ዐቢይ ኮሚቴ አማካኝነት በርካታ ንብረቶች ተመዝግበው ዕውቅና አግኝተዋል።

{አደባባይ ሚዲያ):-

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ግዮን መጽሔት በዛሬ ዕትሟ

ግዮን መጽሔት ዛሬ ቅዳሜ ነሔሴ 16 2018 ዓ.ም ገበያ...

ቱርክ ቤንያሚን ኔታንያሁ ላይ የእስር ማዘዣ አወጣች

ቱርክ የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ ላይ ዓለም አቀፍ...

በመቀለ የሚካሄደው የአሸንዳ በዓል የመክፈቻ ሥነ ሥርዓት ተሰረዘ

በትግራይ በርካታ ታዳሚ በሚገኝበት በየዓመቱ የሚከበረው የአሸንዳ ባህላዊ በዓል...

የኢትዮጵያ ፖስታ 3 ሺሕ የሚጠጉ ቅርንጫፎቹን ወደ ባንክ ኤጀንትነት ለመቀየር እንቅስቃሴ ጀመረ

የኢትዮጵያ ፖስታ በመላ ሀገሪቱ የሚገኙ 3 ሺሕ በሚጠጉ ቅርንጫፎቹ...