አሜሪካ ጨረቃ ላይ የኑክሌር ኃይል ማመንጫ ልትገነባ ነው

Date:

አሜሪካ የኑክሌር ኃይል ማመንጫ ጣቢያ በጨረቃ ላይ ለመገንባት ማቀዷን ፎክስ ኒውስ በዘገባው አስታወቀ።

ናሳ ባለ 100 ኪሎ ዋት የኒውክሌር ጣቢያ ለመገንባት በ60 ቀናት ውስጥ ከኩባንያዎች ተጨባጭ ፕሮፖዛል ሊጠይቅ መሆኑም ተመላክቷል።

በጨረቃ ላይ የሚገነባው የኑክሌር ኃይል ማመንጫ በ2030 አገልግሎት መስጠት እንደሚጀምር ፖሊቲኮ የዜና ድረ-ገጽ ዘግቧል።

የናሳ ተጠባባቂ አስተዳዳሪ ሴን ዱፊ በሚቀጥሉት ቀናት እነዚህን እቅዶች ያሳውቃሉ ተብሎ ይጠበቃል።

ዋና አስተዳዳሪው ለወደፊት የሰው ልጅ የጠፈር ፍለጋ ተልዕኮዎች የጨረቃ እና የማርስ ሃይል አርክቴክቸር አስፈላጊ እና ቀጣይነት ያለው ክፍል መሆኑም ተገልጿል።

ይህን ወሳኝ ቴክኖሎጂ በአግባቡ ለማራመድ የወደፊቱን የጨረቃ ኢኮኖሚ ለመደገፍ፣ በማርስ ላይ ከፍተኛ የሃይል ማመንጨት እና ብሄራዊ ደህንነትን በህዋ ላይ ለማጠናከር ኤጀንሲው በፍጥነት መንቀሳቀስ አለበት ተብሏል።

ይህ ፕሮጀክት የመጣው ከቻይና ጋር ፉክክሩ እጂግ በጣም በጋለበት ወቅት ሲሆን፤ ይህም የመጀመሪያውን ሰው የጨረቃ ተልዕኮ በተመሳሳይ ጊዜ ማከናወን ነው ተብሎለታል።

ይህ እቅድ ከዚህ በፊት በሩሲያ የቀረበ ቢሆንም፤ እስከ አሁን ወደ ስራ አልገባም ተብሏል።

ተንታኞች በጨረቃ ላይ የኒውክሌርየር ማብላያ ሃሳብ አዲስ አይደለም ሲሉም ተደምጠዋል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

የተፈናቀሉ ዜጎች በተጠለሉበት አካባቢ በቋሚነት መኖር የሚያስችላቸው 

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ደቡብ ኦሞ ዞን የዳሰነች ወረዳ ከበኦሞ...

ሻለቃ ኃይሌ ገብረሥላሴ 11ኛውን የኃይሌ ሆቴልና ሪዞርት በደብረ ብርሃን ከተማ አስመረቀ

ታዋቂው አትሌትና ባለሀብት ሻለቃ ኃይሌ ገብረሥላሴ፣ በደብረ ብርሃን ከተማ...

በኢትዮጵያ ሪል ስቴት አልሚዎች ማህበር የተዘጋጀው የመጀመሪያው አህጉራዊ የሪል ስቴት ኤግዘቢሽን ተከፈተ

በኢትዮጵያ ሪል ስቴት አልሚዎች ማህበር አዘጋጅነት የመጀመሪያው አህጉራዊ የሪል...

በሊባኖስ እና በእሰራኤል የተደረሰው የተኩስ አቁም ስምምነት ተራዘመ

ትራምፕ በሊባኖስ እና በእሰራኤል መካከል የተደረሰው የተኩስ አቁም በሦስት...