“አምራች ኢንዱስትሪ የኢኮኖሚ የልብ ምት ነው ” አሕመዲን ሙሐመድ ( ዶ.ር)

Date:

“ኢትዮጵያ ታምርት” ክልላዊ የማጠቃለያ መርሐ ግብር “ኢትዮጵያ ታምርት ለሁለንተናዊ ሉዓላዊነት” በሚል መሪ መልዕክት በኮምቦልቻ ከተማ  ግንቦት 30 2018 ተካሂዷል።

በመርሐ ግብሩ ከባለሃብቶች እና ከባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት ተደርጓል።

በውይይቱ የተገኙ ባለሃብቶች የግብዓት፣ የኀይል አቅርቦት እና የመሠረተ ልማት ዝርጋታ እንዲሟላ ጠይቀዋል። የክልሉን ኢንቨስትመንት ለማሳደግ ሰላምን ማረጋገጥ እንደሚገባም ተናግረዋል።

ክልሉ ተወዳዳሪ እንዲኾን ከተፈለገ ሰላምን ማረጋገጥ እና ለኢንዱስትሪ ማነቆ የኾኑ ችግሮችን መፍታት ይገባል ነው ያሉት። የማስፋፊያ ቦታዎችን ማመቻቸት እንደሚገባም ገልጸዋል።

የፋይናንስ ተቋማት ለባለሃብቶች የብድር አቅርቦት እንዲያመቻቹም ጠይቀዋል።

የአማራ ክልል ኢንዱስትሪ እና ኢንቨስትመንት ቢሮ ኀላፊ እንድሪስ አብዱ የክልሉ ኢንዱስትሪ እና ኢንቨስትመንት ቢሮ ባለሃብቶች የሚያነሷቸውን ችግሮች በዘላቂነት ለመፍታት በትኩረት እየሠራ መኾኑንም ተናግረዋል።

ችግሮች እንዲፈቱ ተደጋጋሚ ውይይቶች እየተደረጉ እና አቅጣጫዎች እየተቀመጡ መኾናቸውንም ገልጸዋል። የፋይናንስ ተቋማት የብድር አቅርቦት እንዲያመቻቹ ውይይት መደረጉንም አንስተዋል። ጥያቄዎችን ደረጃ በደረጃ እንደሚፈቱም ገልጸዋል።

በምክትል ርእሰ መሥተዳድር ማዕረግ የከተማ ዘርፍ አስተባባሪ አሕመዲን ሙሐመድ (ዶ.ር) የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ የኢኮኖሚ መዋቅር ለውጥ ማምጣቱን ገልጸዋል። የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ ችግሮችን እየፈታ፣ የአምራች ኢንዱስትሪዎች ምርት እንዲጨምር ያደረገ ነው ብለዋል።

“አምራች ኢንዱስትሪው የኢኮኖሚው የልብ ምት ነው” ያሉት አስተባባሪው የልብ ምት የኾነውን ዘርፍ በቅንጅት ማሳደግ ይገባል ነው ያሉት። አምራች ኢንዱስትሪው ያለበትን ማነቆ እየፈቱ መሄድ እንደሚገባም አመላክተዋል።

የኀይል አቅርቦትን እና ሌሎች ችግሮችን መፍታት አለብን ነው ያሉት። ከተቋማት ጋር ያለን ቅንጅት ማጠናከር እንደሚያስፈልግም አንስተዋል። ለኢንዱስትሪ የሚመጥን የሰው ኀይል መገንባት እንደሚገባም አመላክተዋል።

ባለሃብቶች ጥራቱን የጠበቀ ምርት እንዲያመርቱም አስገንዝበዋል። በተገቢው መንገድ በመሥራት ኢትዮጵያን ከኢኮኖሚ ጥገኝነት እንዲያላቅቁ እና በሁሉም መስክ ራሷን የቻለች እንድትኾን እንዲተጉም አሳስበዋል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

በከተማዋ ከ24 ሺህ በላይ ንቁ የግንባታ ፈቃድ ያላቸው ሳይቶች መኖራቸው ተገለፀ

በኮንስትራክሽን ዘርፍ የሚደርሰውን የህይወትና የንብረት ጉዳት ለመቀነስ የቁጥጥርና የግንዛቤ...

አትሌት ጉዳፍ ፀጋይ ለሕክምና በወሰደችው መድኃኒት ምክንያት ከውድድር ታገደች

የቀድሞዋ የሁለት ጊዜ የዓለየቀድሞዋፒዮኗ ኢትዮጵያዊቷ ጉዳፍ ፀጋይ ከውድድር በፊት...

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ እውቅና ሊሰጣቸው ነዉ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ እውቅና የሚያገኙት የጎርጎርጎረሳዉያኑ 2026 በሞሮኮ...