አምስት ወደቦች ከባቡር ጋር

Date:


ኢትዮጵያ በዙሪያዋ ያሉ ወደቦችን በባቡር ለማገናኘት የ5 ሺህ ኪሎ ሜትር መስመር ጥናት ማጠናቀቋ ተሰማ

ኢትዮጵያ በርበራ፣ ሞምባሳ፣ ጂቡቲና ፖርት ሱዳንን ጨምሮ በዙሪያዋ ያሉ ሁሉንም ወደቦች በባቡር መስመር ለማገናኘት የ5 ሺህ ኪሎ ሜትር የባቡር መስመር ጥናት ማጠናቀቋን የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር አስታወቀ።

የትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ ሚኒስትር ዴኤታ በርዖ ሐሰን ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ እንደገለጹት፤ ሀገሪቱ በዙሪያዋ ያሉ ወደቦችን በባቡር ለማገናኘት ሰፊ ዕቅድ ይዛ እየሠራች ትገኛለች።

ጥናቱ የተጠናቀቀው የ5 ሺህ ኪሎ ሜትር መስመርም ይህንን የትስስር ዕቅድ ለማሳካት ያለመ መሆኑን አብራርተዋል።

የኢትዮ-ጂቡቲ ባቡር ትራንስፖርት ባለሙያዎች ሥራውን ከተረከቡ በኋላ የጥገና አቅማቸውን እያሳደጉ መሆኑን የገለጹት አቶ በርዖ፤ ወደቦችን ለማገናኘት የተጠኑ አዳዲስ የባቡር መስመሮችም ወደ ተግባር እንዲገቡ አስፈላጊው ጥረት እየተደረገ መሆኑን ገልጸዋል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ምርጫ ለሰላም ግንባታ

ግዮን መጽሔት :-ለኢትዮጵያ ሰላም ምርጫ አማራጭ የሌለው መንገድ ነው።...

ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ከባለፈው  ዓመት የ130 በመቶ ብልጫ  አተረፈ

መጋቢት 30 በተጠናቀቀው የኩባንያው በጀት ዓመት 15.9 ቢሊዮን ብር...

በዕውቀቱ በታላቁ ዓለም አቀፍ ፌስቲቫል ላይ ተመረጠ

ዝነኛው ደራሲና ገጣሚ በዕውቀቱ ሥዩም በስፔን ባርሴሎና በሚካሄደው 41ኛው...