የሰሜን ለንደኑ ክለብ አርሰናል ኤድዊን እና ሆልጄር ኩንቴሮ የተባሉ ኢኳዶራዊ መንትዮች ማስፈረሙን በይፋ አስታውቋል።
መድፈኞቹ ተጨዋቾቹን ከኢኳዶሩ ክለብ ኢንዲፔንዴንቴ ዴል ቫሌ አስፈርመዋል።
መንትዮቹ በአሰልጣኝ ሚኬል አርቴታ የሚመራው አርሰናል የረጅም ጊዜ እቅድ አካል መሆናቸው ተገልጿል።
የ 16ዓመቶቹ መንትዮች በህጉ መሰረት በ 2027 18ዓመት ሲሞላቸው አርሰናልን እንደሚቀላቀሉ ተነግሯል።
ኤድዊን ክንፍ ላይ የሚጫወት የግራ እግር ተጨዋች ሲሆን ፈጣን እና ኳስ የማነከባለል የተለየ ክህሎት የያዘ ተጨዋች ነው።
ሆልጄር በበኩሉ ቴክኒካል ክህሎት የያዘ የአጥቂ አማካይ ተጨዋች መሆኑ ተገልጿል።
@tikvahethsport
