የሁለገቡ ከያኒ ጌትነት እንየው የ68ኛ አመት የልደት በአልና የ43 ዓመታት የሙያ አገልግሎት የምስጋና መርሐ-ግብር በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር ተከብሯል።
ተስፋ የኪነጥበብ ኢንተርፕራይዝ ባዘጋጀው እና በርካታ የጥበብ ቤተሰቦች በተገኙበት ዚህ ልዩ መርሐ-ግብር ላይ —
አቢሲኒያ ባንክ ለከያኒ ጌትነት እንየው 5 ሚሊዮን ብር ስጦታ አበርክቶለታል።
በተጨማሪም ሀበሻ ቢራ አ.ማ የ2025 አዲስ BYD መኪና በስጦታ አበርክቶለታል።
ለ43 ዓመታት ያገለገለው ጌትነት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር ካባ አልብሶታል።
አቢሲኒያ ባንክ በቅርቡ በባህርዳር የሚከፍተውን ቅርንጫፍ ባንክ በጌትነት እንየው ስም መሰየሙን ይፋ አድርጓል።
በዚህ ታላቅ መርሐ-ግብር ላይ የከያኒውን ህይወት የሚያስታውሱ ዝግጅቶችና ምስክርነቶች ተቀርበዋል።
