የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ “ሲ.ቢ.ኢ በጄ” (CBE ByG) የተሰኘ አዲስ የዲጂታል መተግበሪያ አማራጭ በይፋ አስተዋውቋል።
ባንኩ ይፋ ያደረገው ይህ መተግበሪያ ቀደም ሲል ከነበሩት የንግድ ባንክ የዲጂታል አገልግሎቶች በተለየ ይዘት መቅረቡ ተመላክቷል። የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ተጠባባቂ ፕሬዝዳንት የሆኑት አቶ ኤፍሬም መኩሪያ እንዳሉት፣ መተግበሪያው በተለይ ለዲጂታል ብድርና ቁጠባ አገልግሎት የሚውል ነው።
በዚህ መተግበሪያ አማካኝነት ደንበኞች ያለምንም ማስያዣ (Collateral) በዲጂታል የታገዘ የብድር አገልግሎት ማግኘት የሚችሉ ሲሆን፣ መጠኑም ከ500 ብር እስከ 150,000 ብር (አንድ መቶ ሃምሳ ሺህ ብር) ድረስ መበደር እንደሚችሉ ገልጸዋል።
መናኸሪያ ሬዲዮ
