በዓለም ላይ ተወዳጅነትን ያተረፈውን (Twelve Angry Men) የተሰኘውንና በበርካታ ቋንቋዎች የተተረጎመውን ምርጥ ቴአትር አዲስ ተስፋ “አስራ ሁለቱ እንግዶች ” በሚል ርዕስ አዲስ ተስፋ የተረጎመውን ይህን ቴአትር ራሄል ተሾመ አዘጋጅታው በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር ቤት ለእይታ ከበቃ ወራትን አስቆጥሯል::
በኢትዮጵያውያን የቴአትር ተመልካቾች ዘንድ ተወዳጅ የሆነው “አስራ ሁለቱ እንግዶች ” የተሰኝው ይህ አዲስ ቴአትር ዛሬ ነሐሴ 24/5017 ዓ.ም በርካታ ህዝብ በተገኝበት በኢትዮጵያ ብሄራዊ ትያትር አዳራሽ እጅግ በደመቀና በልዩ ዝግጅት ተመርቋል::
አዲስ ተስፋ እጅግ በርካታ ዶክመንተሪ ፊልሞችና የሬዲዮ ድራማዎችንም ፅፏል። የገመና ሁለት ተከታታይ የቴሌቪዥን ድራማ ሃሳብ አመንጪና ደራሲ ሲሆን የፊልም አፃፃፍ ብልሃት የተሰኘም መፅሃፍም ደራሲ ነው :: አዲስ ተስፋ እንኳን ደስ ያለህ!!!
(ይትባረክ ዋለልኝ)
