የቺካጎ ከንቲባ የዶናልድ ትራምፕን ውሳኔ በመቃወም የከተማዋ ፖሊስ ከብሄራዊ ዘቡ ጋር እንዳይተባበር አዘዙ።
የፌደራሉን መንግስት ጣልቃ ገብነት አግባብነት የሌለው ነው ያሉት ከንቲባው መተባበር አያሻንም፤ በራሳችን መወጣት የምንችለውን ጉዳይ ብሄራዊ ዘብ ሀይል ማስፈር ትርጉም የለውም ብለዋል።
የቺካጎ ከንቲባ ብራንዶን ጆንሰን ትራምፕን የተቃወመ ትዕዛዝ ሰተዋል፤ ፊርማቸውንም አሳርፈዋል።
ፖሊስ ከየትኞቹም የፌደራል ሀይሎች ጋር ትብብር እንዳይኖረው የሚከለክለው ውሳኔ ምናልባትም በአሜሪካ ተጨማሪ አለመረጋጋትን እንዳይፈጥር ስጋት ጋርጧል።
ሪፐብሊካኑ ትራምፕ በሚቀጥሉት ቀናት ውስጥ ብሄራዊ ዘቡን ወደ ቺካጎ ሊልኩ እንደሚችሉ እየተነገረ ነው።
ዴሞክራቱ ከንቲባ ጆንሰን ደግሞ ይህን ውሳኔ መቃወማቸው እና አንተባበርም የሚል አቋም ላይ መድረሳቸው በሁለቱ ፓርቲዎች መካከል ፖለቲካዊ እሰጥ አገባው እየበረታ መሄዱን የሚያሳይ ያደርገዋል።
ዶናልድ ትራምፕ በሎስ አንጀለስና ዋሽንግተን ዲሲ ብሄራዊ ዘብ አስፍረው ከተሞችን ተቆጣጥረዋል በሚልም በዴሞክራቶቹ እየተወቀሱ ነው።
ትራምፕ ዴሞክራት ከንቲባዎች በሚያስተዳድሯቸው ከተሞች ላይ ትኩረት አድርገዋል ቢባሉም ከተሞቹን ከወንጀል ነጻ ለማድረግ አማራጩ ይህ ነው ብለውታል።
ከተሞቹ እየሰሩ ያለውን ስራ ግምት ውስጥ ሳያስገባ እንዲሁም ስጋት በሌለበት አጋጣሚ ብሄራዊ ዘቡን ትራምፕ አሰማርተዋል ይላሉ ዴሞክራቶ ሲል ኤን ቢ ሲ ኢንዲያ ቱዴይን ዋቢ በማድረግ ዘግቧል።
