የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የህግ ክፍል ኃላፊ የሆኑት አፈ መምህር አባ ገ/ሥላሴ ጌትነት አቶ ትዝታው ሳሙኤል ከሀገር እንዳይወጣ እግድ እንደተጣለበት በማሕበረ ቅዱሳን ቴሌቪዥን ገለጹ!
እንደ አፈ መምህር አባ ገ/ሥላሴ ገለጻ አቶ ትዝታው ላይ ቤተክርስቲያን ክስ መስርታ ለክሱም ማሰረጃ ይሆናሉ የተባሉትን ፋይሎችን አያይዛ ያቀረበች ሲሆን በዚህም መሰረት ግለሰቡ ከሀገር እንዳይወጣ እገዳ እና በህግ ቁጥጥር ሥር እንዲውል ትዕዛዝ መሰጠቱን ገልጸዋል።
ፖሊስም ግለሰቡን በህግ ቁጥጥር ስር ለማዋል እየፈለገ እንደሆነ በዚህ የፍለጋ ተግባር ላይ የትኛውም ኢትዮጵያዊ እንዲሳተፈ ጥቆማ እንዲያደርግ ጥሪ አቅርበዋል ።
አቶ ትዝታው ሳሙኤል በሚሊኒየም አዳራሸ የኮንሰርት ድግስ ያዘጋጀ መሆኑን የሚታወቅ ሲሆን ለዚህ ዝግጅት መግለጫ ከሌሎች የእምነቱ ተከታዮች ጋር ጭምር መግለጫ መስጠቱ ይታወቃል። በዛሬዉ ቀንም በተዘጋጀው ፕሮግራም ላይ ይገኛል። ታዲያ ፖሊስ ከስፍራው ተገኝቶ ህግን ያሰከብር ይሆን? ግለሰቡንም በህግ ቁጥጥር ሥር ያውለው ይሆን? አብረን የምናየው ይሆናል።
