አቶ አህመድ ሽዴ ከዓለም ባንክ የስትራቴጂክ አጋርነት ኦፕሬሽን ዳይሬክተር ጋር ተወያዩ

Date:


የገንዘብ ሚኒስትር አህመድ ሽዴ ከዓለም ባንክ የኦፕሬሽን ጉዳዮች ማኔጂንግ ዳይሬክተር ሚስ አና ብጄርዴ ጋር በቅድመ-ልማት ፕሮጀክቶች፣ በመካሄድ ላይ ያሉ የሪፎርም ስራዎች እና አዳዲስ የፋይናንሺንግ ዘዴዎች ላይ ያለውን ትብብር ለማጠናከር ከፍተኛ ደረጃ ያለው ውይይት አደርገዋል።

ውይይቱ እ.ኤ.አ ኦክቶበር 2025 ከተካሄደው የዓለም ገንዘብ ድርጅትና የዓለም ባንክ ግሩፕ ዓመታዊ ስበሰባ ጎን ለጎን ነው።

በዚህ ወቅት አቶ አህመድ ሽዴ የዓለም ባንክ የኢትዮጵያን የልማት አጀንዳ ለማሳደግ ያለውን ከፍተኛ ሚና እውቅና በመስጠት እየተደረገ ለሚገኘው የቴክኒክ እና የፋይናንስ ድጋፍ አመስግነዋል።

ባንኩ የኢትዮጵያን ኢኮኖሚ በማዘመን፣ ምርታማነትን በማሳደግ፣ አዳዲስ የእድገት መንገዶችን በመፍጠርና የግሉ ዘርፍ ተሳትፎን በማጎልበት የስራ እድል ለመፍጠር እና የኑሮ ደረጃን ለማሻሻል ያለውን አስተዋፅዖም አንስተዋል።

የዓለም ባንክ ለኢትዮጵያ የረጅም ጊዜ አጋርነት እና ከፍተኛ ድጋፍ እየተካሄዱ በሚገኙ ዋና ዋና ዘርፎች ከ15 ቢሊዮን ዶላር በላይ የሚገመት ድጋፍን በማረጋገጥ ላሳየው አጋርነት ሚኒስትሩ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

የስራ እድል ፈጠራን፣ ዘላቂ መሠረተ ልማቶችንና የሰው ሃይል ልማትን ለማስቀጠል የባንኩ ቀጣይ ተሳትፎ ወሳኝ መሆኑን አጽንኦት ሰጥተው መግለጻቸውም ተመላክቷል።

የኢትዮጵያ መንግስት ባካሄደው የሪፎርም አጀንዳ ምክንያት የተገኘውን ውጤት ያደነቁት የአለም ባንክ ሚስ አና ብጄርዴ፣ በሪፎርሙ አማካኝነት የዋጋ ንረት በከፍተኛ ሁኔታ መቀነሱን፣ ከፍተኛ የወጪ ንግድ መጨመሩን በተለይም በወርቅ የተሻለ የሀገር ውስጥ ገቢ ማሰባሰብ፣ የፊስካል ማገገምን የሚያጠናክር እንዲሁም ከጊዜ ወደ ጊዜ ምቹ የንግድ ሁኔታ እየተፈጠረ መሆኑን ለማሳያነት አንስተዋል።

ዋና ዋና የሪፎርም ርምጃዎችን በመተግበር ረገድ መንግስት የጀመረውን እንቅስቃሴ አጠናክሮ እንዲቀጥል እንደሚያበረታቱም መግለፃቸውን የዘገበው ኢዜአ ነው

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

የተፈናቀሉ ዜጎች በተጠለሉበት አካባቢ በቋሚነት መኖር የሚያስችላቸው 

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ደቡብ ኦሞ ዞን የዳሰነች ወረዳ ከበኦሞ...

ሻለቃ ኃይሌ ገብረሥላሴ 11ኛውን የኃይሌ ሆቴልና ሪዞርት በደብረ ብርሃን ከተማ አስመረቀ

ታዋቂው አትሌትና ባለሀብት ሻለቃ ኃይሌ ገብረሥላሴ፣ በደብረ ብርሃን ከተማ...

በኢትዮጵያ ሪል ስቴት አልሚዎች ማህበር የተዘጋጀው የመጀመሪያው አህጉራዊ የሪል ስቴት ኤግዘቢሽን ተከፈተ

በኢትዮጵያ ሪል ስቴት አልሚዎች ማህበር አዘጋጅነት የመጀመሪያው አህጉራዊ የሪል...

በሊባኖስ እና በእሰራኤል የተደረሰው የተኩስ አቁም ስምምነት ተራዘመ

ትራምፕ በሊባኖስ እና በእሰራኤል መካከል የተደረሰው የተኩስ አቁም በሦስት...