በፀሐፌ ትዕዛዝ አክሊሉ ሀብተወልድ የልጅነት ታሪክ ላይ ያተኮረ ለታዳጊዎች የሚሆን መፅሀፍ ታትሞ ገበያ ላይ ዋለ።
የመፅሀፉ ደራሲና አሳታሚ የህክምና ዶክተር ሰላማዊት ታደሠ ስትሆን መፅሀፉም 63 ገፆች አሉት።
መፅሐፉ የራሱ መዝገበ ቃላት ያለውና የሽፋንና የውስጥ ገፆች ሰዓሊውም የ15 ዓመት ዕድሜ ያለው የደራሲዋ ልጅ ናታንያ አብርሀም ነው።
ደራሲዋ እንደምትናገረው ይህ አሁን ገበያ ላይ የዋለው መፅሐፍ ከ4ቱ ተከታታይ መፅሐፍት ውስጥ የመጀመሪያው ክፍል ነው።
ደራሲዋ ከዚህ ቀደም አክሊሉ በሚል ርዕስ በጠቅላይ ሚኒስትር አክሊሉ ሀብተወልድ ላይ ያተኮረ ታሪካዊ ልቦለድ ፅፋ፣ ማሳተሟና ማስመረቋ ይታወቃል።
አሁን ደግሞ ታዳጊ ልጆች የበለጠ ስለ ኢትዮጵያዊያን የአገር ባለውለታዎች እንዲያውቁ ይህን ለታዳጊዎች ይሆናል ያለችውን መፅሐፍ ለማሳተም መቻሏን ደራሲዋ ተናግራለች።
መፅሀፉ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በተዘጋጀው የመፅሐፍ ኤግዚብሽን ላይ እየተሸጠ እንደሚገኝ ለማወቅ ተችሏል።
