አደራ ጠባቂው የሚድሮኩ ወንድም ጀማል !

Date:

ሚድሮክ የሚለውን ስም ሁላችንም እናውቀዋለን። ኢትዮጵያ ውስጥ ያልተሰማራበት መስክ አለ ማለት ያዳግታል። በሰማይም በየብስም በባህርም የሚሰሩ ስራዎች ላይ ሼህ አልአሙዲን አሉ፣ እሳቸው ካሉ ሚድሮክ አለ፣ ሚድሮክ ካለ ከ 74000 በላይ ሰራተኞችና ከነሱ ጀርባ ደግሞ በሚሊየኖች የሚቆጠር ቤተሰብ አለ።

ሚድሮክ ግዙፍ ነው። ሚድሮክ የሐገር ጌጥ፣ የድሆች መጠለያ፣ የበጎ አድራጎቶች ቁንጮ፣ በሺዎች የሚቆጠሩ ቤተሰቦች የገቢ ምንጭ እንዲሁም ከፍተኛ ግብር ከፋይ ሆኖ ከሁለት አስርት አመታት በላይ የቆየ አንጋፋ ድርጅት ነው።

ነገር ግን ድርጅቱም ሆነ የድርጅቱ ባለቤት ላይ በገጠመ ችግር ድርጅቱ ላይ ከፍተኛ የሆነ አደጋ እንደደመና አንዣበበ።
ችግሩ ብዙ ነው። ከድርጅቱ ግዙፍነት አንፃር፣ ካለው ከፍተኛ የሃብት መጠንና የሰራተኛ ብዛት አንፃር፣ ከተሰማራበት መጠነ ሰፊ የኢንቨስትመንት መስክና ከጀመራቸው እልፍ አእላፍ ፕሮጀክቶች አንፃር ለዚያ የሚመጥን ማኔጅመት ባለመኖሩ ምክኒያት ብዙ ድርጅቶቹ አደጋ ውስጥ ወደቁ።

ሼህ እልአሙዲን ከሳውዲ እንዳይወጡ በመደረጋቸው ምክኒያትና በተለያየ ጫና ለአመታት የለፉበትን ድርጅት በቅርበት ሊከታተሉ ባለመቻላቸውና እዚ የተቀመጡት ማኔጅመንቶች ደግሞ በከፍተኛ ቸልተኝነትና የግል ጥቅምን በመጋበስ ስራ ውስጥ በመጠመዳቸው 74 ሺ ሰራተኛን የተሸከመ የሐገር ምሰሶ ዘመም ማለት ጀመረ። ዝርፊያው ተጧጧፈ፣ ሙስናው ሰፋ፣ ብክነቱ የድርጅቱን መሰረት ነቀነቀ፣ ትልልቅና ግዙፍ ድርጅቶች ሊሸጡ ነው የሚል ወሬ መስተጋባት ጀመረ። አደራ ጠባቂ ተብለው የተቀመጡ ብዙዎች አደራቸውን በሉ። የ ሰባ አራት ሺ ሰራተኛ ህይወትና ከነሱ ጀርባ ያሉ ሚሊየኖች ላይ…..ተቀለደ።

“ሳይደግስ አይጣላም” እንዲሉ አበው….

የዚህ ግዜ ነው አቶ ጀማል አዲሱ CEO ሆኖ ድንገት ብቅ ያለው። አቶ ጀማል የሼሁን ጫማ እየለካ ያደገ፣ ሼሁን እንደአርአያ ሲመለከት የኖረ አላህን የሚፈራ ጉልበተኛ ወንድም ነው።

ጀማል አደራውን ጠበቀ። በአጭር ግዜ ውስጥም ተአምር ሰራ። ከፍተኛ የሆነ የአስተዳደር እርምጃዎችን ወሰደ። ያዘመሙ ግዙፍ ድርጅቶች በሁለት እግራቸው ዳግም ቆሙ! ከዚያም አልፈው ከፍተኛ ትርፋማ ሁኑ። በኪሳራ ሊሸጡ ነው የተባሉ ድርጅቶች ሳይቀር አይተው የማያውቁትን ትርፍ ማግኘት ጀመሩ። ሰራተኛ ሊቀንስ ነው የተባለው ሚድሮክ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰራተኞች መቅጠር ጀመረ። ፕሮጀክቶችን ሊያቋርጥ ነው የተባለ ድርጅት አዳዲስ ፕሮጀክቶችን ጀመረ።

አቶ ጀማል አደራን የመወጣት ምሳሌ ሆነ። የሰባ አራት ሺ ሰራተኛ ህይወትንና ከነሱ ጀርባ ያለን ሚሊዮን ሰው ህይወት ታደገ። ጭራሽ ሚድሮክ ኢትዮጵያንና ሚድሮክ ቴክኖሎጂን ከሆራይዘን ኢትዮጵያ ጋር አዋሃደ፣ ከዚያም ታላቁን ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕን ፈጠረ። አርባ አምስት የተበታተኑ ድርጅቶችን ወደስድስት በመሰብሰብ ለእየአንዳንዱ ብቁ ማኔጅመንቶችን በመመደብ ታላቁን Resurrection በአጭር አመት ውስጥ ሰርቶ አሳየ! እንደኤልፎራ ያሉ ከሃያ አመት በላይ በኪሳራ ሲሰሩ የነበሩ ድርጅቶች በአጭር ግዜ ውስጥ በዶሮ ምርት ከምስራቅ አፍሪካ አንደኛ ሆኑ!

ታማኙ አቶ ጀማል የሚመራው ሚድሮክ ዛሬ ኢትዮጵያ ውስጥ ትልቁ የገቢም የወጪም ምርት ከመንግስት ልማት ድርጅቶችም በላይ አምራች ነው። ትልቁ ኤክስፖርተር ነው። ትልቁ ደሞዝ ከፋይ ነው። ትልቁ ግብር ከፋይ ነው። ብቸኛው የወርቅ ኮሜርሻል ማይነር ነው። ሻይ ቅጠል፣ ቡና ፣ አበባ፣ የቆዳ ምርቶችን ወዘተ ሳይቀር ለተለያዩ አለማት የሚልክ እጅግ ትርፋማ ድርጅት ሆኖ ቀጠለ።

አቶ ጀማል በዚህ አላበቃም። ባለቤት እንደሌለው ሲዘረፍ የነበረውን የሚሊየኖችን ቤት ያቆመ ድርጅት ዝርፊያውን አስቁሞ ብቻ አልተቀመጠም። ኢትዮጵያ ውስጥ በመንግስት ለሚካሄዱ ትልልቅ “ዜጋ ተኮር” ፕሮጀክቶች ከፍተኛ በጀት በመመደብ ከድሆች ጎን ቆመ። ድሃ የሚወድ ሰው ክብር አለው። አቶ ጀማል ጠቅላይ ሚኒስትሩም እንደመሰከሩለት አይነት ሰው ነው። ባጭሩ ሼህ መሀመድን የሚያኮራ፣ ሐገርን የሚያስጠራ፣ ለሚሊየኖች አለኝታ የሆነን ድርጅት ፈጥሮ አሳየ።

አደራ ጠባቂው አቶ ጀማል ብዙ ሊከበርና ሊደነቅ የሚገባው ሰው ሆኖ አግኝቸዋለሁ። ሰው ማለት የወደቀን የሚያነሳ፣ ሃላፊነቱን የሚያውቅ፣ ላመነው ሰው እምነቱን ሳይሸራርፍ የሚወጣ ፣ በሐገር ፍቅር የተለከፈ፣ ሰራተኞቹን የሚወድ፣ ለደሃ የሚራራ ማለት ነው።

ክብር ለሚገባው ክብር እንሰጣለን! የአቶ ጀማልን ሙሉ ኢንተርቪው ያድምጡት https://youtu.be/g2QH8kPV47M?si=ad6A-i0ffAYqL1Sh

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

አለሁ እኔ ለወገኔ የድጋፍ ጥሪ

እሺ ምን እናድርግ? አርሲ ብቻ ሳይሆን ኦርቶዶክሳዊነት ወንጀል የሆነባቸው አካባቢዎች...

በኢትዮጵያ ከ1.6 በመቶ በላይ የሚሆነው ሕዝብ ከፍተኛ የእይታ ችግር አለበት

በኢትዮጵያ ከ1.6 በመቶ በላይ የሚሆነው ሕብረተሰብ ከፍተኛ የእይታ ችግር...

3ኛው የሩሲያ – አፍሪካ ጉባኤ በሞስኮ ይጀምራል

ጥቅምት 28 እና 29 እ.ኤ.አ.3ኛው የሩሲያ - አፍሪካ ጉባኤ...

ዳሸን ባንክ  “ዳሸን ኤር ፔይ” የተሰኘ  የክፍያ አገልግሎት አስተዋወቀ

  ዳሸን ባንክ ለንግድ ተቋማትና ለደንበኞች ግብይትን በተቀላጠፈ መልኩ ለማከናወን...