በቻይናውያን ባለሀብቶች ባለቤትነት የተያዘው ቲክቶክ በአሜሪካ ገዢ እየፈለገ ባለበት በአሁኑ ወቅት የአሜሪካ እና የቻይና ባለሥልጣናት ሰኞ ዕለት በስፔን የንግድ ድርድር ማድረግ መጀመራቸውን ቢቢሲ ዘግቧል።
ድርድሩ የሚመራው በአሜሪካው የግምጃ ቤት ኃላፊ ስኮት ቤሴንት እና የቻይናው ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ሂ ላይፌንግ ሲሆኑ፣ በሁለቱ ግዙፍ ኢኮኖሚ ባላቸው አገራት መካከል የንግድ ጦርነት እንዳይቀሰቀስ ለማድረግ ጥረት ያደርጋሉ።
ዶናልድ ትራምፕ በመጀመሪያው የሥልጣን ዘመናቸው ወቅት ቲክቶክ እንዲታገድ ሲወተውቱ የነበረ ሲሆን፣ አሁን ግን ይህንን አቋማቸውን በመቀየር ለሦስት ጊዜ ያህል መተግበሪያው የሚታገድበትን ጊዜ አራዝመዋል።
ትራምፕ እሁድ ዕለት ለጋዜጠኞች እንዳሉት ” እንዲሞት ልንተወው [ቲክቶክን] እንችላለን። ወይንም ደግሞ… አላውቅም። ሁኔታዎች አሁን በቻይና ላይ የተመሠረተ ነው። ብዙም ግድ የሚሰጥ ጉዳይ አይደለም ” ብለዋል።
ቲክቶክ በአሜሪካ የሚታገድበት የመጨረሻው ቀን የፊታችን ረብዕ ነው።
ለአራተኛ ጊዜ እግዱ ሊራዘም ይችላል የሚል ተስፋ አለ።
ባለፈው ወር ፕሬዝዳንት ትራምፕ ገዢ እስኪገኝ ድረስ የሚዘጋበትን ቀን ሊያራዝሙ እንደሚችሉ ተናግረዋል።
መተግበሪያው በመላው ዓለም ቢሊዮኖች የሚጠቀሙበት ሲሆን፣ በአሜሪካ ብቻ 170 ሚሊዮን ተጠቃሚዎች አሉት።
በዚህ ሳምንት ልዑካን ቡድኑ ከተወያየ በኋላ ትራምፕ እና የቻይናው ፕሬዝዳንት ዢ ጂንፒንግ በጥቅምት ወር ተገናኝተው ስለሚወያዩባቸው ጉዳዮች ያነጋገራል ተብሎ ይጠበቃል።
የቀኑ መራዘም ሁለቱ አገራት ” ፍትሐዊ ያልሆነ የንግድ ተግባራት ” ባሉት ላይ ለመደራደር ዕድል የሚሰጣቸው ሲሆን፣ የብሔራዊ ደኅንነት ጉዳዮች ተነስተው ውይይት እንደሚደረግባቸው ዋይት ሐውስ አስታውቋል።
BBC
