አዲሱ የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ስትራቴጂ ለአረንጓዴ ኢኮኖሚ ሽግግር አቅም ይሆናል

Date:

አዲሱ የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ስትራቴጂ ለአረንጓዴ ኢኮኖሚ ሽግግር አቅም እንደሚሆን የስራና ክህሎት ሚኒስትር ዴዔታ ተሻለ በሬቻ(ዶ/ር) ገለጹ፡፡

ጠንካራ የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ተቋማትን በመገንባት በእውቀትና ክህሎት የበቃ የሰው ኃይል ማፍራት የሚያስችል አዲስ የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ስትራቴጂ ተዘጋጅቶ ስራ ላይ መዋሉ ይታወቃል።

የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ዴዔታ ተሻለ በሬቻ(ዶ/ር) ለኢዜአ እንዳሉት፤ አዲሱ ስትራቴጂ የአረንጓዴ የክህሎት ልማት የስልጠና ፕሮግራሞችን የያዘ እና ለታዳሽ ኃይል ትኩረት የሰጠ ነው።

ወደ አረንጓዴ ኢኮኖሚ በሚደረገው ሽግግር ብቃትና ክህሎት ያለው የሰው ኃይል ወሳኝ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ስትራቴጂው ብቃት ያለው እና ለአካባቢ ተስማሚ ቴክኖሎጂዎችን የሚተገብርና ሃብትን በቁጠባ የሚጠቀም ትውልድ ለመገንባት እንደሚያስችል ገልጸዋል፡፡

ሥርዓተ-ትምህርቶችን በአረንጓዴ የስራ መርሆዎችና አሠራሮች በማበልጸግ ተማሪዎች ከተቋማት ሲወጡ ለአካባቢ ተስማሚ የሆኑ ዘዴዎችንና መሣሪያዎችን እንዲጠቀሙ ያስችላል ብለዋል፡፡

አዲሱ የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ስትራቴጂ ለአረንጓዴ ኢኮኖሚ ሽግግር አቅም እንደሚሆንም ነው ሚኒስትር ዴዔታው የተናገሩት፡፡

በአዲሱ የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ስትራቴጂ መሰረት የአረንጓዴ ቴክኒክና ሙያ ልጠና ፓኬጅ ተቀርጾ ወደ ስራ መግባቱን አመላክተዋል፡፡፡

ይህ ፓኬጅ ከብክለትና ከብክነት የጸዳ የሃይል አጠቃቀም እንዲኖር ያስችላል ብለዋል፡፡

በተቋማት ውስጥ ዘመናዊ እና ለአካባቢ ተስማሚ የሆኑ የማሰልጠኛ መሣሪያዎችን በማስገባት ተማሪዎች በዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ እንዲሆኑ እንደሚሰራም ተናግረዋል፡፡

ተማሪዎች በንድፈ ሃሳብ ብቻ ሳይሆን በዘመናዊ አረንጓዴ ቴክኖሎጂዎች ተግባራዊ ልምምድ በማድረግ በሥራ ዓለም ውስጥ የአረንጓዴ ልምዶችን የመተግበር ብቃት እንዲኖራቸው እየተደረገ መሆኑንም ገልጸዋል፡፡

ከዓለም አቀፍ የአረንጓዴ ኢኮኖሚ መስፋፋት ጋር ተያይዞ የሚፈጠሩ አዳዲስ የስራ ዕድሎችን መጠቀም እንደሚያስችልም እንዲሁ፡፡ ዘገባው የኢዜአ ነው።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

በከተማዋ ከ24 ሺህ በላይ ንቁ የግንባታ ፈቃድ ያላቸው ሳይቶች መኖራቸው ተገለፀ

በኮንስትራክሽን ዘርፍ የሚደርሰውን የህይወትና የንብረት ጉዳት ለመቀነስ የቁጥጥርና የግንዛቤ...

አትሌት ጉዳፍ ፀጋይ ለሕክምና በወሰደችው መድኃኒት ምክንያት ከውድድር ታገደች

የቀድሞዋ የሁለት ጊዜ የዓለየቀድሞዋፒዮኗ ኢትዮጵያዊቷ ጉዳፍ ፀጋይ ከውድድር በፊት...

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ እውቅና ሊሰጣቸው ነዉ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ እውቅና የሚያገኙት የጎርጎርጎረሳዉያኑ 2026 በሞሮኮ...