አዲስ አበባ ለአስር ያህል የተፈጥሮ እና ሰዉሰራሽ አደጋዎች ተጋላጭ መሆኗ ተገለፀ

Date:

መዲናይቱ ለጎርፍ ፥ መሬት መንሸራተት ፥  የህንፃ መደርመስ እና እሳት ላሉ የአደጋ ክስተቶች ተጋላጭ መሆኗን ጥናት አሳይቷል።

በአዲስአበባ እሳት እና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮምሽን የአደጋ ቅነሳ ዘርፍ ሀላፊ የሆኑት አቶ ደሳለኝ ቱፋ የከተማዋን የአደጋ ስጋት በተመለከተ በኮተቤ ዩንቨርስቲ ጥናት መደረጉን ይገልፃሉ።

ሃላፊዉ ይህ ጥናት እንደገለፀዉ ከሆነም አዲስ አበባ አስር ለሚደርሱ የተፈጥሮ እና ሰዉሰራሽ የአደጋ ክስተቶች ተጋላጭ መሆኗን ጠቁሟል ብለዋል።

ከተማዋ በዋነኝነት ለጎርፍ ተጋላጭ መሆኗን የሚገልጹት ሀላፊዉ በመጪዉ የክረምት ወራት ዉስጥ ኮምሽኑ ተጋላጭ ቦታዎችን መለየቱን ተናግረዋል።

2 መቶ 38 አካባቢዎች ለጎርፍ እና ለመሬት መንሸራተት ተጋላጭ እንደሆኑ ተለይተዋል ያሉት አቶ ደሳለኝ ቱፋ 98 የሚሆኑን አካባቢዎች ለቅድመ አደጋ መከላከል ስራ እንዲሰራባቸዉ ለባለድርሻ አካላት ከምክረ ሀሳብ ጋር ተላልፎል ብለዋል።

የመሬት መንሸራተት ስጋት በታየባቸዉ አካባቢዎች እርምጃዎች እየወሰድን ነዉ የሚሉት ሀላፊዉ የጎርፍ ስጋት የሚያስከትሉ ክስተቶችን ለማስወገድ እየተሰራ ነዉ ይላሉ።

ከተማ አስተዳደሩበአዲስ አበባ በመጪው የክረምት ወቅት ጎርፍ ቢያጋጥም ክፍለ ከተሞች ተጠያቂ እንደሚሆኑ መነገሩ ይታወሳል።

በቅርቡ በተካሄዱት የኮሪደር ልማት ስራዎች ወቅት ሳይታዩ የታለፉ ወይም የተዘጉ የጎርፍ መውረጃዎች ካሉ፣ ክረምቱ ከመግባቱ በፊት በፍጥነት መለየትና ምላሽ መስጠት እንደሚገባ ማሳሰቢያም ተሰጥቷል

በዛሬዉ እለት የ2018 የበጀት አመት የስራ አፈፃፀም ሪፖርቱን  የአዲስ አበባ የእሳት እና አደጋ ስጋት አመራር ኮምሽን አቅርቧል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

የኢራን ጠቅላይ መሪ ለአባታቸው ግድያ “የበቀል እርምጃ” እንደሚወሰድ ተናገሩ

የኢራን ጠቅላይ መሪ ሞጅታባ ኻሜኒ በጽሑፍ ባስተላለፉት መልዕክት አባታቸው...

የኢትዮጵያ ከ17 ዓመት በታች ሴቶች ብሔራዊ ቡድን የመጨረሻ ልምምዱን ሰርቷል

ቡድኑ ነገ የአለም ዋንጫ ማጣሪያ የመጨረሻ ዙር የመልስ ጨዋታውን...

ኢራን ከአሜሪካ ጋር ለመደራደር አለመጠየቋን አስታወቀች

የኢራን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ኢስማኤል ባጋይ፤ አገራቸው...

ሱዳን ዉስጥ ለሦስት ዓመታት የተካሄደው ጦርነትን ሰለ ማቆም

የሱዳን ብሔራዊ ጦር ለሦስት ዓመታት የተካሔደውን ጦርነት ለማቆም አሜሪካ...