አዲስ የሴራሚክ ፋብሪካ ከ3 ሳምንት በኋላ ምርት ማምረት ይጀምራል

Date:

በ50 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር ኢንቨስትመንት ከአዲስ አበባ 65 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በምትገኘው በቱለፋ ከተማ የተገነባው ይህን ፋብሪካ የገነባው ባይጂያ ሴራሚክ ማኑፋክቸሪንግ  የተባለ ድርጅት ነው።

በ30 ሄክታር መሬት ላይ ያረፈው ይህ የሴራሚክ እና የፖርስሊን ምርቶች ፋብሪካ ምርት ሲጀምር ብቻውን አሁን ካለው የሴራሚክ ፍላጎት እስከ 70 በመቶ ድረስ የማቅረብ አቅም አለው ተብሎለታል።

በባይጂያ ሴራሚክ ማኑፋክቸሪንግ የሚመረቱን ምርቶች ለገበያ የሚያቀርበው ማንሰን ኢንቨስትመንትስ  ነው።

የማንሰን ኢንቨስትመንትስ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ዳዊት እርገቱ እና የባይጂያ ሴራሚክ ማኑፋክቸሪንግ ዋና ስራ አስኪያጅ ጃንግ ሁዋ ይህኑን ለማድረግ የሚያስችላቸውን ስምምነት ተፈራርመዋል።

ስመምነቱ  ማንሰን ኢንቨስትመንትስ ለኢትዮጵያ ገበያ ተስማሚ የሆኑ እና በልዩ ሁኔታ ዲዛይን የተደረጉ የሴራሚክ እና የፖርስሊን ምርቶችን በባይጂያ ሴራሚክ ማኑፋክቸሪንግ አማካኝነት በኢትዮጵያ ለማስመረት እና በብቸኝነት ለማከፋፈል ያስችለዋል ተብሏል፡፡

ባይጂያ ሴራሚክ ማኑፋክቸሪንግ በበኩሉ ምርቶቹን በማንሰን ቴክኒካዊ ደረጃዎች፣ የምርት ስያሜ (ብራንድ) መስፈርቶች እና የገበያ ዝርዝር መመሪያዎች መሰረት ምርቶቹን የማምረት ኃላፊነት  እንዳለበት ተነግሯል።

ስምምነቱ ከውጭ የሚገቡ ምርቶችን በሀገር ውስጥ በመተካት የውጪ ምንዛሪ ፍሰትን በመቀነስ እና ጥራት ያላቸው የሴራሚክ ምርቶች በኢትዮጵያ እንዲመረቱ በማድረግ ሀገሪቱ የያዘቸውን የኢንዱስትሪ ልማት እቅድ ይደግፋል ተብሎ ታምኖበታል፡፡

ባይጂያ ሴራሚክ ማኑፋክቸሪንግ የሚያመርታቸውን ሴራሚክስ እና ፖርስሊን ምርቶችን ለገበያ ለማቅረብ የተስማማው ማንሰን ኢንቨስትመንትስ  አራዳ ሞል እና በብሔራዊ ቤተ መንግሥት የተነገባውን ምናብ ዌልነስ የሰራ ድርጅት መሆኑን ሰምተናል።

ንጋቱ ( ሸገር 102.1)

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ሻለቃ ኃይሌ ገብረሥላሴ 11ኛውን የኃይሌ ሆቴልና ሪዞርት በደብረ ብርሃን ከተማ አስመረቀ

ታዋቂው አትሌትና ባለሀብት ሻለቃ ኃይሌ ገብረሥላሴ፣ በደብረ ብርሃን ከተማ...

በኢትዮጵያ ሪል ስቴት አልሚዎች ማህበር የተዘጋጀው የመጀመሪያው አህጉራዊ የሪል ስቴት ኤግዘቢሽን ተከፈተ

በኢትዮጵያ ሪል ስቴት አልሚዎች ማህበር አዘጋጅነት የመጀመሪያው አህጉራዊ የሪል...

በሊባኖስ እና በእሰራኤል የተደረሰው የተኩስ አቁም ስምምነት ተራዘመ

ትራምፕ በሊባኖስ እና በእሰራኤል መካከል የተደረሰው የተኩስ አቁም በሦስት...

ከ 50 ሚሊዮን በላይ መራጮች በማንዋልና በዲጂታል ተመዝግበዋል

ከየካቲት 28_መጋቢት 28 የመራጮች ምዝገባ ሲካሄድ እንደነበር ይታወቃል። በተለያዩ ጉዳዮች...