አፍሪካ የአሜሪካ ዶላር የበላይነትን ለመገዳደር ያደረገችው ጥረት የመጀመሪያ ፍሬዎችን ጀምሯል

Date:

የአፍሪካ ሀገራት የአሜሪካን ዶላር በደረጃ በመተው በምትኩ የቻይናውን ዩዋን እና የሀገር ውስጥ ገንዘቦችን መጠቀማቸውን እያሳደጉ እንደሚገኙ ዘ ኢኮኖሚስት ዘግቧል።

ዛምቢያ አሁን የማዕድን ሮያሊቲ (የባለቤትነት) ክፍያዎችን በዩዋን መቀበል የጀመረች ሲሆን፣ ለአገር ውስጥ የንግድ ልውውጦች የሀገር ውስጥ ገንዘብ ብቻ ጥቅም ላይ እንዲውል አስገዳጅ ደንብ አውጥታለች (ሕጉን በሚጥሱት ላይ የገንዘብ መቀጮ ወይም የእስራት ቅጣት ይጣላል)፡፡

ግብፅ፣ ናይጄሪያ እና ደቡብ አፍሪካ አዳዲስ የዩዋን የገንዘብ ልውውጥ ስምምነቶችን የተፈራረሙ ሲሆን፤ ኬንያ የዶላር ብድሮቿን ወደ ዩዋን በመቀየር በዓመት ወደ 215 ሚሊዮን ዶላር ገደማ የሚጠጋ የወለድ ወጪ መታደግ ችላለች፡፡

በሀብት መጠኑ የአፍሪካ ትልቁ ባንክ የሆነው “ስታንዳርድ ባንክ” በቻይና ድንበር ተሻጋሪ የባንኮች የክፍያ ስርዓት በኩል የመጀመሪያዎቹን ክፍያዎች የፈጸመ ሲሆን፤ በአፍሪካ በዩዋን የሚደረጉ ድንበር ተሻጋሪ ክፍያዎች እ.ኤ.አ. ከ2020 እስከ 2024 ባለው ጊዜ ውስጥ በ4 እጥፍ አድገዋል፡፡

የመላው አፍሪካ የክፍያ ስርዓት (ፓፕስ) ከአኅጉሪቱ ውስጣዊ የንግድ ልውውጦችን በሀገር ውስጥ ገንዘቦች ለመፈጸም በአሁኑ ወቅት ከ160 በላይ ባንኮችን ያገናኘ ሲሆን፣ ይህም በዓመት እስከ 5 ቢሊዮን ዶላር ሊታደግ እንደሚችል ይጠበቃል።

ይህ ሽግግር ሙሉ በሙሉ አልጋ በአልጋ አይደለም፤ ኩባንያዎች በዶላር የገቧቸውን ውሎች እንደገና ማስተካከል አለባቸው፤ ላኪዎች የገንዘብ ምንዛሬ ክፍያዎችን ይጋፈጣሉ፤ እንዲሁም ጥቂት ኢንዱስትሪዎች ለገቢ ንግድ የሚያስፈልጋቸውን ዶላር የማግኘት እጥረት ያጋጥማቸዋል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

የታሰሩ የፖለቲካ ታጋዮች እንዲፈቱ ተጠየቀ

ትብብር ለኢትዮጵያ አንድነት መንግሥት በጠባብ ቀዳዳ የምታየውን የፖለቲካ ምኅዳር...