ኢራን በትራምፕ ላይ የግድያ ሙከራ ልትፈጽም ማቀዷን እስራኤል አሳወቀች

Date:

እስራኤል፣ ኢራን በአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ላይ የግድያ ሙከራ ለማድረግ ማቀዷን የሚያሳይ የደህንነት መረጃ ለአሜሪካ መንግስት ማጋራቷ ተገለጸ።

ኢራን ትራምፕን ለመግደል ያጠነጠነችው ሴራ በእስራኤል የስለላ ድርጅት ተደርሶበት ለአሜሪካ መረጃው እንደተላለፈ የአሜሪካ መገናኛ ብዙሀን ዘግበዋል።

ምንም እንኳን የአሜሪካ እና የኢራን ባለስልጣናት ለዚህ ዘገባ እስካሁን ይፋዊ ምላሽ ባይሰጡም፤ ዋሽንግተን ከዚህ ቀደም የቴህራንን በርካታ የደህንነት ስጋቶችና በትራምፕ ላይ የተቃጡ የግድያ ሙከራዎችን ማክሸፏን መግለጿ ይታወሳል።

ከሰሞኑ በቱርክ በተካሄደው የኔቶ ጉባኤ ላይ የተገኙት ትራምፕ፤ ወደ ሀገራቸው ለመመለስ ሲነሱ የተሳፈሩበትን አውሮፕላን በድንገት መቀየራቸውም ከዚሁ የደህንነት ስጋት ጋር በተያያዘ እንደሆነ ተነግሯል።

የአሜሪካ የደህንነት መስሪያ ቤት ባስተላለፈው የጥንቃቄ መመሪያ መሰረት፤ የቀድሞው አውሮፕላን የሚሳኤል ጥቃቶችን አቅጣጫ የሚያስቱና ከራዳር እይታ የሚሰውሩ ዘመናዊ ወታደራዊ የደህንነት ሲስተሞች የተገጠሙለት በመሆኑ፤ አሁን ካለው የጥቃት ስጋት አንጻር ይበልጥ አስተማማኝ ሆኖ ተመርጧል።

የአውሮፕላን ቅያሬው አዲሱን አውሮፕላን ቀድሞ በማስነሳት በእንግሊዝ ለሚገኙ የአሜሪካ ወታደሮች ለማሳየት የተደረገ መደበኛ አሰራር ነው በማለት ስጋቱን ለማስተባበል ቢሞከርም፤በጉዞው ወቅት በአውሮፕላኑ ውስጥ የነበሩ ጋዜጠኞችና ተሳፋሪዎች ግን መስኮቶችን ዝግ አድርገው እንዲቆዩ ጥብቅ መመሪያ ተሰጥቷቸው ነበር ሲል ሲኤንኤን ዘግቧል።

የዋይት ሀውስ ቃል አቀባይ በበኩላቸው፤ ቀጣናው በርካታ ጠላቶች ያሉበት በመሆኑ አሜሪካ ፕሬዝዳንቷን ለመጠበቅ የምትችለውን አቅም ሁሉ እንደምትጠቀም አስታውቀዋል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

የኢራን ጠቅላይ መሪ ለአባታቸው ግድያ “የበቀል እርምጃ” እንደሚወሰድ ተናገሩ

የኢራን ጠቅላይ መሪ ሞጅታባ ኻሜኒ በጽሑፍ ባስተላለፉት መልዕክት አባታቸው...

የኢትዮጵያ ከ17 ዓመት በታች ሴቶች ብሔራዊ ቡድን የመጨረሻ ልምምዱን ሰርቷል

ቡድኑ ነገ የአለም ዋንጫ ማጣሪያ የመጨረሻ ዙር የመልስ ጨዋታውን...

ኢራን ከአሜሪካ ጋር ለመደራደር አለመጠየቋን አስታወቀች

የኢራን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ኢስማኤል ባጋይ፤ አገራቸው...

ሱዳን ዉስጥ ለሦስት ዓመታት የተካሄደው ጦርነትን ሰለ ማቆም

የሱዳን ብሔራዊ ጦር ለሦስት ዓመታት የተካሔደውን ጦርነት ለማቆም አሜሪካ...