የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮምሽን ባህርዳር ቅርንጫፍ በበጀት አመቱ 9 ወራት 163 አቤቱታዎች ተቀብያለሁ ብሏል።
የቅርንጫፍ ፅህፈት ቤቱ ሀላፊ አቶ አለባቸው ብርሃኑ ከደረሱ አቤቱታዎች 15 ያህሉ ብቻ መፍትሄ እንዲያገኙ መደረጉን ተናግረዋል።
ፅህፈት ቤቱ በማረሚያ ቤቶች፣ በፖሊስ ጣቢያዎችና ክትትል በሚያስፈልጋቸው ሌሎች ቦታዎች ላይ ክትትል እያደረገ እንደሚገኝ ሀላፊዉ ገልፀዋል።
ሆኖም በርካታ ማረሚያ ቤቶች በክልሉ ቢኖሩም በበጀት ዓመቱ ክትትል የተደረገባቸዉ አምስት ማረሚያ ቤቶች ናቸዉ ተብሏል።
የሕዝብ ተወካዮች ም/ ቤት የዴሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ በበኩሉ በማረሚያ ቤቶች እያደረገ የሚገኘው የክትትልና ምርመራ ስራ ከክልሉ ነባራዊ የፀጥታ ሁኔታ አንጻር ሲታይ መልካም የሚባል ነዉ ሲል ገልፆል።
በክልሉ ከሰብዓዊ መብቶች አኳያ የሚፈጠሩ ጥሰቶች በየትኛው፤ አካል ይፈፀሙ ምርመራ እንደሚደረግ ፅህፈት ቤቱ አንስቷል።
የኢሰመኮ ባህር ዳር ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ተደራሽነቱን በማስፋት የክትትል እና ምርመራ ስራውን አጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የዴሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ገልፆል።
