ኢትዮጵያ ሀብተማርያም የHYBE America ፕሬዝዳንት ሆና ተሾመች

Date:

በዓለም አቀፍ የሙዚቃ ኢንዱስትሪ ውስጥ ስሟ በጉልህ የሚነሳው ኢትዮጵያ ሀብተማርያም፣ የታዋቂው የBTS አሳታሚ HYBE America የሙዚቃ ዘርፍ ፕሬዝዳንት በመሆን  ተሹማለች።

በዚህ ስራዋ ኢትዮጵያ በሎስ አንጀለስ እና የአሜሪካ የሙዚቃ ማዕከል በሆነችው አትላንታ ላይ መሰረቷን በማድረግ ስራዋን የምትሰራ ሲሆን በኩባንያው ስር ያሉ የሙዚቃ አሳታሚዎችን  የመምራት፣ አዳዲስ ተሰጥኦዎችን የመመልመል እና የኩባንያውን የንግድ እድሎች የማስፋት ስራንም ታከናውናለች።

ይህ ሹመት HYBE በአሜሪካ ያለውን ተደራሽነት ለማጠናከር እና የጥቁር አሜሪካውያንን (R&B እና Hip-Hop) ባህል ከዓለም አቀፉ ገበያ ጋር ለማስተሳሰር ያለመ ነው።

ኢትዮጵያ ሀብተማርያም ​የታዋቂውን Motown Records በሊቀመንበርነት እና በዋና ስራ አስፈጻሚነት መርታለች።

እንደ Lil Baby, Migos, Lil Yachty እና City Girls ያሉ ዝነኛ አርቲስቶችን በማሳደግ ረገድ ትልቅ ስራ ሰርታለች።

በUniversal Music Group ውስጥ በቆየችባቸው 20 ዓመታት ከነ Justin Bieber, J. Cole እና Chris Brown ጋር ሰርታለች።

የHYBE America ዋና ስራ አስፈጻሚ አይዛክ ሊ፦ “ኢትዮጵያ በሙዚቃው ዓለም ላይ ያላት እይታ እና ስልታዊ ብልህነት ወደር የማይገኝላት ያደርጋታል” ሲሉ አድንቀዋታል።

​ኢትዮጵያ በበኩሏ፦ “HYBE አርቲስቶችን እና አድናቂዎችን የሚያገናኝበት መንገድ ለረጅም ጊዜ ስታዘበው የነበረ ድንቅ ስራ ነው። በዚህ ጉዞ ውስጥ የራሴን ልምድ ለማበርከት በመመረጤ ደስተኛ ነኝ” ብላለች።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ለ10 ምሁራን የሙሉ ፕሮፌሰርነት ማዕረግ ሰጥቷል

የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ አስተዳደር ቦርድ ጥቅምት 12 ቀን 2019...

ዳሸን ባንክ እና ሼባ ማይልስ የፕላቲንየም ብራንድ የማስተር ካርድ ይፋ አደረጉ

ዳሸን ባንክ እና ሼባ ማይልስ በኢትዮጵያ ለሚገኙ ደንበኞች የፕሪሚየም...

የአሜሪካ የደህንነት ኃላፊ ኢራንን አስጠነቀቁ

ቡሔራዊ ደህንነት ዳይሬክተር ጄይ ክላይተን አርብ ዕለት ኢራን በውጭ...

ኢትዮጵያ በግብርናው ዘርፍ  በአመት ከ1.1 ቢሊዮን ዶላር በላይ ታጣለች

85 በመቶ የሚሆነው የኢትዮጵያ ህዝብ በግብርናው ዘርፍ የተሰማራ ሲሆን...