አፍሪካ በብራዚል ቤሌም ከተማ በተካሄደው የ2025ቱ የተመድ የአየር ንብረት ለውጥ ኮንፈረንስ (COP 30) ላይ በአንድ ድምፅ ተናግራለች፤ ዓለምም ሰምቷታል።
የሰው ልጅ ከሚያጋጥሙት እጅግ ከባድ ተግዳሮቶች አንዱ የሆነውን ችግር ለመፍታት የሚደረገውን የጋራ ጥረት እንድንመራ ለተሰጠን ዕድልም እናመሰግናለን።
የዓለም አቀፉ ማኅበረሰብም እንዲህ ያለ ወሳኝ ኃላፊነት ስለሰጠንም ክብር ይሰማናል።
ይህ እውቅና ኢትዮጵያ በአየር ንብረት ለውጥ ላይ ባሳየችው የመሪነት ሚና እና ዋና ዋና ዓለም አቀፍ ዝግጅቶችን የማስተናገድ አቅሟ ላይ ያላችውን እምነት የሚያንፀባርቅ ነው።
ኢትዮጵያ እ.አ.አ በ2027 በአዲስ አበባ የሚካሄደው COP 32 ጠንካራ እና ትርጉም ያለው ውጤት እንዲያስመዘግብ እና በአየር ንብረት ለውጥ ላይ የጋራ እርምጃዎችን ለመውሰድ ምቹ ሁኔታን ለመፍጠር በቁርጠኝነት ትሰራለች።
አፍሪካ የመፍትሔ አህጉር መሆኗን እና በዓለም አቀፍ ጥረቶች ውስጥ ቁርጠኛ አጋር መሆኗን ለማሳየት ኢትዮጵያ የመሪነት ሚናዋን መጫወት ትቀጥላለችም፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር)
