የህዝብ ተወካዮች የሰው ሃብት ልማት ሥራ ስምሪትና ቴክኖሎጂ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የትምህርት ዘርፉን የ1ኛ ሩብ ዓመት ሥራ አፈፃፀም በተመለከተበት ወቅት የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ በከፍተኛ ትምህር ተቋማት የክብር ዶክትሬት አሰጣጥን ችግር የነበረበት በመሆኑ ወጥ አሰራር መከተል በማስፈለጉ የክብር ዶክትሬት አሰጣጥን ሀገራዊ መመሪያ ተዘጋጅቶ ለትግበራ ዝግጁ ሆኗል፡፡
ሁሉም የከፍተኛ ትምህርት ተቋም በመመሪያው መሰረት ተፈፃሚ ማድረግ ያለባቸው ሲሆን የክብር ዶክትሬት ማዕረግ የሚያገኙ ሰዎች ዶክተር ወይንም የክብር ዶክተር በሚል መጠሪያነት መጠቀም እንደማይቻል አሳስበዋል።
የከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የክብር ዶክትሬት ማዕረግ ለመስጠት ሀገራዊ እና አለም አቀፍ መስፈርቶችን ማሟላት እንዳለባቸው በመመሪያው ተካቷል፡፡
በሙያው የተለየ ስራ ያበረከተ ኢትዮጵያዊም ሆነ ሌላ ዜጋ በመመሪያው የተዘረዘረውን መስፈርት የሚያሟላ ከሆነ የክብር ዶክትሬት ማዓረግ ማግኘት እንደሚችል ጠቅሰው ይሁን እንጂ የተሠጠውን የክብር ዶክትሬት ለመጠሪያነት መጠቀም እንደማይቻል አብራርተዋል።
