ኢትዮጵያ በቢሊዮን ዶላር የሚቆጠር ዓለም አቀፍ የካሳ ክስ አሸነፈች

Date:

በሄግ የሚገኘው ቋሚ የግልግል ዳኝነት ፍርድ ቤት በቱርኩ አክጉን ኢንሻዓት የኮንስትራክሽን ኩባንያ እና በኢትዮጵያ መንግሥት መካከል ለዓመታት ሲካሄድ የቆየውን የቢሊዮን ዶላር የካሳ ክርክር በኢትዮጵያ አሸናፊነት አጠናቋል።

ኩባንያው በ1,500 ሄክታር መሬት ላይ ሊያርፍ የነበረውን “የኢትዮ-ቱርክ ዓለም አቀፍ የኢንዱስትሪ መንደር” ፕሮጀክት መንግሥት አግዶብኛል በሚል ከ1 ቢሊዮን ዶላር በላይ የካሳ ጥያቄ አቅርቦ የነበረ ቢሆንም፣ ፍርድ ቤቱ ጥያቄውን ሙሉ በሙሉ ውድቅ አድርጎታል።

የኢትዮጵያ መንግሥት የፕሮጀክቱን ግንባታ ያገደው የአካባቢው መገኛ ለለገዳዲ ግድብና ለከተማዋ የውሃ ማጣሪያ ጣቢያ ደህንነት ስጋት መሆኑን በጥናት በማረጋገጡ እንደሆነ ያስረዳ ሲሆን፣ ፍርድ ቤቱም ይህ የውሃ ሀብትን የመጠበቅ እርምጃ ተገቢና የሁለትዮሽ የኢንቨስትመንት ስምምነትን የማይጥስ መሆኑን አምኖበታል።

በዚህም መሠረት ኢትዮጵያ ለዲዛይንና ለቅድመ ዝግጅት ሥራዎች የወጡ አነስተኛ ወጪዎችን ብቻ እንድትከፍል ተወስኖባታል።

ይህ ውሳኔ ሀገሪቱ ብሔራዊ ጥቅሟንና የተፈጥሮ ሀብቷን ለማስከበር ለምትወስደው ሕጋዊ እርምጃ ትልቅ ዓለም አቀፍ ድል ተደርጎ ተወስዷል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

በከተማዋ ከ24 ሺህ በላይ ንቁ የግንባታ ፈቃድ ያላቸው ሳይቶች መኖራቸው ተገለፀ

በኮንስትራክሽን ዘርፍ የሚደርሰውን የህይወትና የንብረት ጉዳት ለመቀነስ የቁጥጥርና የግንዛቤ...

አትሌት ጉዳፍ ፀጋይ ለሕክምና በወሰደችው መድኃኒት ምክንያት ከውድድር ታገደች

የቀድሞዋ የሁለት ጊዜ የዓለየቀድሞዋፒዮኗ ኢትዮጵያዊቷ ጉዳፍ ፀጋይ ከውድድር በፊት...

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ እውቅና ሊሰጣቸው ነዉ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ እውቅና የሚያገኙት የጎርጎርጎረሳዉያኑ 2026 በሞሮኮ...