ኢትዮጵያ ባለፉት 6 ዓመታት ዓለማቀፍ የልማት ግቦችን እያሳካች እንደሆነ ተነገረ

Date:

አፈ ጉባኤው ኡዝቤኪስታን በሚካሄደው 150ኛ ዓለማቀፍ የፓርላማ ሕብረት ጉባኤ ላይ ተሳትፎ እያደረጉ ነው፡፡

አፈ ጉባኤው አገኘሁ ተሻገር በጉባኤው ላይ ባደረጉት ንግግር ኢትዮጵያ ከ2030 የዘላቂ ልማት ግቦች እና ከአፍሪካ አጀንዳ 2063 ጋር የተጣጣመ የአሥር ዓመት ሀገራዊ የልማት ዕቅድ አውጥታ እየሠራች እንደምትገኝ አብራርተዋል።

ባለፉት ስድስት ዓመታት ዓለም አቀፍ የልማት ግቦችን በማሳካት ረገድ ከፍተኛ ውጤት እያሳየች እንዲሁም ፈጣን የኢኮኖሚ እድገት እያስመዘገበች እንደሆነም በንግግራቸው ጠቁመዋል፡፡

የኢትዮጵያ ፓርላማ የሚሊኒየሙን የዘላቂ ልማት ግቦች ለማሳካት የተለያዩ ፖሊሲዎች፣ ፕሮግራሞችና የሕግ ማዕቀፎችን መርምሮ በማፅደቅ፣ ክትትልና ድግፍ በማድረግ የሚጠበቅበትን ኃላፊነት እየተወጣ ይገኛል ማለታቸውን የፌዴሬሽን ምክር ቤት አስታውቋል፡፡

@sputnik_ethiopia

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ከ989 ሚሊዮን ብር በላይ የኮንትሮባንድ እቃዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ

የጉምሩክ ኮሚሽን ከግንቦት 27 እስከ ሰኔ 3 ቀን 2018...

“እኔ እስካለሁ ድረስ ኢራን የኑክሌር መሣሪያ ባለቤት አትሆንም!”

የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ ትናንት ሰኔ 5 ቀን...

አገር እንዲህ ዓይንህን ለአፈር ይባላል?

በተጀመረው የአለም ዋንጫ ደቡብ አፍሪካ በሜክሲኮ መሸነፏን ተከትሎ አፍሪካ...

አሜሪካ እና ኢራን የመጀመሪያ ደረጃ ስምምነት በ24 ሰዓት ውስጥ እንደሚፈራረሙ ፓኪስታን አስታወቀች

ዩናይትድ ስቴትስ እና ኢራን በሰላም ድርድሩ ማዕቀፎች ላይ መስማማታቸውን...