የኢትዮጵያና የፈረንሳይ መንግስታት የኢትዮጵያን የኢኮኖሚ ማሻሻያ የሚደግፉ ታሪካዊ ስምምነቶችን ተፈራርመዋል።
ስምምነቱን የኢትዮጵያ የገንዘብ ሚኒስትር አቶ አህመድ ሽዴ እና በፈረንሳይ የአውሮፓና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ ሚስዝ ኤሌኖሬ ካሮይት ተፈራርመዋል።
ስምምነቱ የዕዳ ሽግሽግ (Debt Restructuring): በG20 የጋራ ማዕቀፍ ስር ከሁለትዮሽ አበዳሪዎች ጋር የተደረገ የመጀመሪያው ታሪካዊ የዕዳ ሽግሽግ ስምምነት ተፈርሟል።
እንዲሁም ለሁለተኛው የሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ (HGER 2.0) ማስፈጸሚያ የሚውል 80 ሚሊየን ዩሮ የበጀት ድጋፍ እና 1.5 ሚሊየን ዩሮ የቴክኒክ ድጋፍ ስምምነት መደረጉን ኢቢሲ ዘግቧል።
በተጨማሪም ፈረንሳይ በኢትዮጵያ በሚገነባው የቢሾፍቱ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ግንባታ ላይ ለመሳተፍ ፍላጎት አሳይታለች።
በአሁኑ ወቅት በኢትዮጵያ ያለው የፈረንሳይ አጠቃላይ የኢንቨስትመንት መጠን ከ600 ሚሊየን ዩሮ በላይ የደረሰ ሲሆን፥ ከዚህ ውስጥ ከግማሽ በላይ የሚሆነው (300 ሚሊየን ዩሮ) ለኢነርጂ ዘርፍ መዋል መቻሉ ተገልጿል።
