የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በተያዘው 2018 ዓ.ም ለሚያከናውነው 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ የቅድመ-ምርጫ ተግባራት ሲከናወን መቆየቱ ይታወሳል።
ቦርዱ እስካሁን ስለሠራቸው የቅድመ-ምርጫ ሥራዎች በተመለከተና በተያያዥ ጉዳዮች ዙሪያ ለመገናኛ ብዙኃን ተቋማትና ጋዜጠኞ የካቲት 5 ቀን 2018 ዓ.ም ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥቷል።
ቦርዱ ግንቦት 24 ቀን 2018 ዓ.ም የሚያከናውነው ጠቅላላ ምርጫ 109 ቀናት ብቻ የቀሩት መሆኑን በመግለጫዉ ላይ አንስቷል።
መግለጫዉ በዋናነት የመራጮች ምዝገባ ያለበት ሁኔታን ለማሳወቅ መሆኑን የገለፁት የቦርዱ ሰብሳቢ ሜላተ ወርቅ ሀይሉ በዚህም የመራጮች ምዝገባ ቀን መራዘሙን ገልፀዋል።
ከዚህ ቀደም በወጣዉ ፕሮግራም መሠረት የመራጮች ምዝገባ ከየካቲት 7 እስከ መጋቢት 7 የነበረ ቢሆንም ይህ ቀኑ መራዘሙን ገልፀዋል።
በዚህ መሠረትም የመራጮች ምዝገባ የካቲት 28 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ የሚከናወን መሆኑን ሰብሳቢዋ ገልፀዋል።
የእጮች ምዝገባም በተመለከተ ፖርቲዎች ሲያነሱ የነበረዉ ቅሬታ ለመፍታት ስራዎች መሠረታቸዉን የገለፁ ሲሆን ለተጨማሪ እገዛ በሚል የቦርዱ ባለሙያዎች ለፖርቲዎች እርዳታ አሰየሰጡ መሆኑን ገልፀዋል።
የእጮች ምዝገም በተመሳሳይ እስከ የካቲት 16 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ መራዘሙ የሚታወስ ነዉ።
