ኢትዮጵያ ከአሜሪካ የቀረበላትን አዲሱን የታሪፍ አወቃቀር ተቀበለች

Date:

ኢትዮጵያ ከአሜሪካ የቀረበላትን አዲሱን የታሪፍ አወቃቀር በደስታ እንደምትቀበል አስታወቀች። ይህ አወቃቀር የኢትዮጵያ ምርቶች ወደ አሜሪካ ገበያ ሲገቡ የሚጣልባቸውን ታሪፍ 10% ብቻ በማድረግ ተወዳዳሪነታቸውን ያሳድጋል ብሏል።

መንግስት ይህ ውሳኔ በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን የንግድ ግንኙነት ለማጠናከር እና የኢትዮጵያን ኤክስፖርት ለማሳደግ ወሳኝ እርምጃ መሆኑን ገልጿል።

የገንዘብ ሚኒስቴር ዉሳኔዉን ተከትሎ እንዳስታወቀዉ ይህ አዲሱ የታሪፍ አወቃቀር ኢትዮጵያ እንደ ቬትናምና ባንግላዴሽ ካሉ ትልልቅ የማምረቻ ማዕከላት ጋር ስትወዳደር የተሻለ እድል እንዲኖራት ያደርጋል።

“የ10% የታሪፍ መጠን ለኢትዮጵያ ላኪዎች ከፍተኛ ማበረታቻ ይሰጣል” ሲል ሚኒስትሩ አስታውቋል ። “ይህ የኢትዮጵያ ምርቶች በአሜሪካ ገበያ ተወዳዳሪ ዋጋ እንዲኖራቸው በማድረግ የፍላጎት እና የኢንቨስትመንት መጨመርን ያመጣል ሲል ተስፋዉን ጥሏል።

ይሁን እንጂ፣ የዘርፉ ባለሙያዎች እንደሚያስጠነቅቁት፣ ይህንን እድል በአግባቡ ለመጠቀም ኢትዮጵያ አሁንም በርካታ ተግዳሮቶችን መወጣት አለባት። የመሠረተ ልማት ውስንነት፣ የምርት ጥራት እና ደረጃዎች፣ የውጭ ምንዛሪ እጥረት እና የፖለቲካ አለመረጋጋት ጥቂቶቹ መሆናቸውን አፅንኦት ሰጥተዉ ተናግረዋል።

Source: capitalethiopia

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ግዮን መጽሔት በዛሬ ዕትሟ

ግዮን መጽሔት ዛሬ ቅዳሜ ነሔሴ 16 2018 ዓ.ም ገበያ...

ቱርክ ቤንያሚን ኔታንያሁ ላይ የእስር ማዘዣ አወጣች

ቱርክ የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ ላይ ዓለም አቀፍ...

በመቀለ የሚካሄደው የአሸንዳ በዓል የመክፈቻ ሥነ ሥርዓት ተሰረዘ

በትግራይ በርካታ ታዳሚ በሚገኝበት በየዓመቱ የሚከበረው የአሸንዳ ባህላዊ በዓል...

የኢትዮጵያ ፖስታ 3 ሺሕ የሚጠጉ ቅርንጫፎቹን ወደ ባንክ ኤጀንትነት ለመቀየር እንቅስቃሴ ጀመረ

የኢትዮጵያ ፖስታ በመላ ሀገሪቱ የሚገኙ 3 ሺሕ በሚጠጉ ቅርንጫፎቹ...