ኢትዮጵያ ዕዳ የመክፈል ጫና ውስጥ መሆኗን የአለም ባንክ እና አይ ኤም ኤፍ ገለጹ

Date:

የዓለም ባንክ እና የዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት (አይ.ኤም.ኤፍ) በጋራ ባካሄዱት አዲስ ግምገማ፣ ኢትዮጵያ ዕዳ የመክፈል ጫና ውስጥ መሆኗን አስታወቁ። ሪፖርቱ፤ ሀገሪቱ “ያልተረጋጋ የመበደር እና ዕዳ የመመለስ አቅም ላይ ናት” ሲል በመግለጽ፤ በኢኮኖሚ ላይ ጥብቅ ማሳሰቢያ ሰጥቷል።

በሁለቱም ተቋማት ከፍተኛ ባለሥልጣናት የጸደቀው ሪፖርቱ፣ “ኢትዮጵያ ከኤክስፖርት የምታገኘው ገቢ በቂ ባለመሆኑ ዕዳዋን የመመለስ አቅሟ የተዳከመ ነው” ብሏል። አክሎም፣ ሀገሪቷ የቦንድ ሽያጭ ክፍያዋን መክፈል ካልቻለችበት ታኅሣሥ 2023 ጀምሮ በዕዳ ጫና ውስጥ መሆኗን ገልጿል።

የተቋማቱ ግምገማ፤ የኢትዮጵያን የዕዳ መክፈል ችግርን ያባባሰው በአጭርና መካከለኛ ጊዜ ውስጥ የሚከፈል የዕዳ መጠን መብዛት እና በትግራይ ጦርነት ወቅት እና ከጦርነቱ በኋላ ከውጭ የሚገኝ የገንዘብ ድጋፍ በከፍተኛ ሁኔታ መቀነሱ መሆኑን አመላክቷል።

ሪፖርቱ፤ “የማሻሻያ አጀንዳ በወቅቱ መተግበር እና ከውጭ አበዳሪዎች የሚገኝ የዕዳ እፎይታ የገንዘብ እጥረትን ለማቃለል እና የዕዳዋን ለመቆጣጠር ይረዳል” ብሏል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

የተፈናቀሉ ዜጎች በተጠለሉበት አካባቢ በቋሚነት መኖር የሚያስችላቸው 

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ደቡብ ኦሞ ዞን የዳሰነች ወረዳ ከበኦሞ...

ሻለቃ ኃይሌ ገብረሥላሴ 11ኛውን የኃይሌ ሆቴልና ሪዞርት በደብረ ብርሃን ከተማ አስመረቀ

ታዋቂው አትሌትና ባለሀብት ሻለቃ ኃይሌ ገብረሥላሴ፣ በደብረ ብርሃን ከተማ...

በኢትዮጵያ ሪል ስቴት አልሚዎች ማህበር የተዘጋጀው የመጀመሪያው አህጉራዊ የሪል ስቴት ኤግዘቢሽን ተከፈተ

በኢትዮጵያ ሪል ስቴት አልሚዎች ማህበር አዘጋጅነት የመጀመሪያው አህጉራዊ የሪል...

በሊባኖስ እና በእሰራኤል የተደረሰው የተኩስ አቁም ስምምነት ተራዘመ

ትራምፕ በሊባኖስ እና በእሰራኤል መካከል የተደረሰው የተኩስ አቁም በሦስት...